2012-08-27 15:09:28

ብፁዕ ካርዲናል ቱራን፦ ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካና የሃይማኖት ነፃነት


Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” ዓመታዊው የጥናት ጉባኤ እንደተለመደው እ.ኤ.አ. ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊሊያ ሮማ አቅራቢያ በምተገኘው ሪሚኒ ከተማ በማዘጋጀት ዘንድሮ “የሰው ልጅ ዓይነተኛው ባህርይ ከወሰን አልቦ ጋር ተገናኝነት በተሰየመው ጠቅላይ ርእስ ሥር የማኅበርሰቡ መሥራች RealAudioMP3 ስመ ጥር ነፍሰ ኄር ክቡር አባ ልዊጂ ጁሳኒ ሃይማኖታዊ ስሜትና ትርጉም” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት አቢይ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ጥናታዊ ሰነድ ላይ በማተኮር ቀጥሎ ያካሄደው የዘንድሮ 33ኛው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ትላትና እ.ኤ.አ. ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. አጠናቋል።
በመዝጊያው ቀን ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ቱራን የኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ጁሊዮ ተርዚ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ሊቀ መንበር ናሲር አብዱልአዚዝ አል-ናሰር ባሳተፈው “ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካና የሃይማኖት ነፃነት’ በሚል ርእስ ዙሪያ በተካሄደው ክፍለ ውይይት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ በፓኪስታን ሃይማኖት በማርከስ ወንጀል ተከሳ በእስር ላይ የምትገኘው ማንበብና መጻፍ ገና ያልተማረች በአካልና አእምሮ ሰንካይ በሽታ የተጠቃች የአገሪቱ ዜጋ ታዳጊ ወጣት ጉዳይ ባሰሙት ንግግር በማስታወስ፣ “አለ እግዚአብሔር የሆነው ዓለም መገንባት ዓለምን ኢሰብአዊነት ማድረግ ማለት ነው። ሰው በባህርዩ ሃይማኖተኛ ነው። ስለዚህ የሃይማኖት ነፃነት እንዲከበር ማድረግ ይኽንን ዓይነተኛው ባህርዩን መንከባከብ ማለት መሆኑም አስረድተው፣ የሃይማኖት ነፃነት የሰው መሆናዊው ባህርይ የሚጠይቀው ለተቀሩት የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት ነው። እንዳሉ ዓወደ ጥናቱን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታውቀዋል።
በናይጀሪያ እንዲሁም በተለያየ ሥፍራ ተከስቶ ያለው ጸረ ክርስትያን ዓመጽ አሳሳቢ መሆኑም ብፁዕነታቸው ሲገለጡ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ሊቀ መንበር ናሲር አቡዱልአዚዝ አል-ናስር፣ በዓለማችን የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ማጠናከር እጅግ አስፈልጊ መሆኑ ሲያብራሩ፣ የኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ተርዚም በዓረብ አገሮች እየተቀጣጠለ ያለው ጸደይ ተብሎ የሚነገርለት ህዝባዊ ንቅናቄ ለሃይማኖት ነፃነት ዋስትና እንዲሆን ኢጣሊያ በመዲትራኒያን ክልል የምታነቃቃው አመለካከት መሆኑ ገልጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ 33ኛው ዓለም አቀፍ “Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የጥናት ጉባኤ እ.ኤ.አ. ቀጣዩ 34ኛው ዓለም አቀፋዊው ዓወደ ጥናቱን እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 18 እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. አንገብጋቢ ሰብአዊነት” በሚል ዋና ርእስ ሥር ለማካሄድ በመወሰን ማጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ገልጠው፣ በዚህ በዘንድሮው ዓለም አቀፋዊው ዓውደ ጥናት ከ 40 አገሮች የተወጣጡ ስምንት መቶ ሺሕ ሰዎች መሳተፋቸው አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.