2012-08-27 15:04:01

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ “ቤተ ክርስትያን አንድ በክርስቶስ የተወሃደ ለዓለም ክፍት የሆነ ማኅበረሰብ ነች”


በካስተል ጋንዶልፎ እንደተለመደው በየዓመቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ የሐወልት ምስል በማስቀደም በመርከቦች ታጅቦ የሚከናወነው መንፈሳዊ ዑደት ባለፈው ቅዳሜ መፈጸሙ ሲገለጥ፣ ለዚህ ቅዱስ ባህል 35ኛው ዓመት ጅማሬ ምክንያት አንድ ቀን በማስቀደም በካተል ጋንዶልፎ በሚገኘው በቅድስት ድንግል ማርያም RealAudioMP3 ዘሓይቅ በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የተመራ መሥዋዕት ቅዳሴ መቅረቡ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት “ቤተ ክርስትያን አንድ በክርስቶስ የተወሃደ ለዓለም ክፍት የሆነ ሌሎችን ለማስተናገድ ምሉእ ብቃት ያለው ማኅበርሰብ ማለት ነች” በማለት ቤተ ክርስትያንን እንደገለጡትም አመልክተዋል።
“የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስትያን፦ በአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት ለዓለም ክፍት የሆነ የሱታፌ ምሥጢር” በማለት እንደሚገልጣትም አስታውሰው፣ የዛሬ 35 ዓመት ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ 6ኛ የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ የሐወልት ምስል በማስቀደም በካስተል ጋንዶልፎ በሚገኘው ሐይቅ በተናንሽ መርከቦች ታጅቦ የሚፈጸመው መንፈሳዊ ዑደት ምእመናን ወደ ምድረ ተስፋ ወደ ሆነው የዘለዓለማዊው ሕይወት ባህር ዳርቻ ለመድረስ በዚህ በዓለም ባህር የሚያከናወን ጉዞ ተምሳይ መሆኑ ሰጥተዉት የነበረው የዚህ የካተል ጋንዶልፎ መንፈሳዊው ዑደት ትርጉም መሆኑ ገልጠው፣ እንዲሁም “ሁለ-መናቸው የማርያም” በማለት ለሚገልጡዋቸው ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. መስከረም 2 ቀን 1979 ዓ.ም. በካተል ጋንዶልፎ ተገኝተው በቅድስት ድንግል ማርያም ዘሓይቅ ቤተ ክርስትያን ለክብሯ ያቀረቡት መሥዋዕተ ቅዳሴ ማስታወሳቸውንም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.