2012-08-27 15:11:35

በይሎሩሲያ፦ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ የመገናኛ ብዙሃን ጉባኤ


የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የመገናኛ ብዙሃን ህላዌና መጻኢ በሚል ርእስ ሥር በበይሎሩይስ ህሮድና ከተማ ወደ ተጀመረው የሦስት ቀን ጉባኤ የማኅበራዊ ግኑኝነት ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ እንዲሁም የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል RealAudioMP3 ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በድምጽና ምስል የተቀረጸ መልእክት ማስተላለፋቸው ተገልጠዋል።
አዳዲስ የተራቀቁ የእደ ጥበብ ግኝቶች የክርስትና እምነት በበለጠ ለማስፋፋት ለአስፍሆተ ወንጌል አመች እንደሆነም ብፁዕ አቡነ ቸሊ ባስተላለፉት የድምጽና ምስል መልእክት ሲያሰምሩበት፣ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በበኵላቸውም መገናኛ ብዙሃን ለውይይትና ለሱታፌ ያለው ሚና ላይ በማተኮር ቤተ ክርስትያን የተቀበለችው ተልእኮ የመገናኛ ብዙሃን ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያደርጋት መሆኑ አብራርተው፣ በመገናኛው ብዙሃን በኩል የምታስተላልፈው መልእክት አማካኝነት ለሁሉም ቅርብ በመሆን በተለይ ደግሞ የአዲሱ የእደ ጥበብ እድገት ፈጣን ተጠቃሚው ለሆነው ወጣት ያላት ቅርበት የሚያጎለብት ነው። ቤተ ክርስትያን ተገናኝነት ዓይነተኛ ባህርይዋ ነው። ስለዚህ ለሌሎች የምታካፍለው መልእክት የቃል ብቻ ሳይሆን፣ በምስክርነት ጭምር የተሸኘ ወንድማማችነት ፍትህ ዕርቅ ሰላም የመሳሰሉት አበይት እሴቶች በማስፋፋት ሕዝብን በማነጽ ቀለል ባለ አገላለጥ፣ ሰው ከየት ወዴት ለሚለው መሠረተታዊ ጥያቄ መልሱን ለሁሉም የምታብራራበት መሣሪያ ነው ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ በበይሎሩሲያ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ የቫቲካን ረዲዮ የመርሃ ግብር ጉዳይ አስተዳዳሪ አባ አንድረዘይ ኮፕሮቪስኪ እየተሳተፉ ናቸው።







All the contents on this site are copyrighted ©.