2012-08-23 10:29:50

በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕረፍት ምክንያት የተላከ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የሐዘን መግለጫ መልእክት


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ በብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በኩል ለኢትዮጵያ መንግሥት ርእሰ ብሔር ግርማ ወልደግዮርጊስ የሐዘን መልዕክት ልከዋል፣ ቅዱስነታቸው ለበርካታ ዓመታት ኢትዮጵያን በመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ- ሕይወት የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን ገልጠው ለቤተ ሰቦቻቸውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥናቱ እንዲሰጣቸው በላኩት የሐዘን መልእክት አመካይነት ገልጠዋል፣
ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት የመሯት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባደረባቸው ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወት ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ በእጅጉ ማሳዘኑ ከአዲስ አበባ የሚደርሱ ዜናዎች ያመለክታሉ። ማክሰኞ ምሽት ላይ አስከሬናቸው ከብሩሰል በልጅዩም ሴንት ሉክ ሆስፒታል አዲስ አበባ ገበተውል። የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ባለ ሥልጥናት የሃይማኖት መሪዎችና ብዙ ሕዝብ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ያላቸውን አክብሮትና ፍቅር እንዲሁም የተሰማቸውን መሪር ሐዘን ገለጠዋል፣
የኢትዮጵያ ፌደራል ዲሞክራቲክ ረፓብሊክ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና ረዳት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃለማርያም ደሳለኝ ተጠብባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በሙሉ ስልጣን ሀገሪቱን እየመሩ መሆናቸው የመንግስት ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ ዋና ሐላፊ አቶ በረከት ስምዖን ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል፣
በጠቅላይ ሚኒስትር ሕልፈተ ሕይወት ምኽንያት ከየዓለም ሀገራት መሪዎች የሐዘን መግለጫ ወደ አዲስ አበባ እየጐረፈ መሆኑ ተመልክተዋል፣
ከዚህ በመቀጠል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕልፈተ ሕይወት ትኩረት የሰጠ ከሊቃ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ እና የጳጳሳት ጉባኤ ፕረሲዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ያካሄድነው ቃለ ምልልስ ለማዳመጥ ትችላላችሁ፣ RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.