2012-08-22 12:56:16

የር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ዓመታዊ ክብረ በዓል


ኩላዊት ቤተ ክርስትያን በላቲን ሥርዓት ትላትና ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዳከበረች ሲገለጥ፣ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ( እ.ኤ.አ. ሰነ 2 ቀን 1835 ዓ.ም. - ነሐሴ 20 ቀን 1941 ዓ.ም.) እ.ኤ.አ. በ 1903 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ተሹመው ቤተ ክርስትያንን ለረዥም RealAudioMP3 ዓመታት በቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሓዋርያዊ መሪነት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 20 ቀን 1941 ዓ.ም. በሰማያዊ ቤት እስከ ተወለዱበት ቀን ድረስ ለክርስቶስ እውነት ያገለገሉ መሆናቸው የሚያወሳው የቤተ ክርስትያን ታሪክ እ.ኤ.አ. በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ሰነ 3 ቀን 1951 ዓ.ም. ብፅዕና ከታወጀላቸው በኋላ እ.ኤ.አ. ግንቦት 29 ቀን 1954 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ቅድስና እንዳወጀችላቸውም ያመለክታል።
የዛሬ ሁለተ ዓመት በፊት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ላቀረቡት ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ ርእስ በማድረግ ባስደመጡት አስተምህሮ፣ “ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የመዳን እቅድ ጥበብ ለሁሉም ግልጽ እንዲሆን የፈጸሙት ያልታከተ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የደረሱት የትምህርተ ክርስቶስ መጽሓፍ ተጨባጭ ምስክር ነው። የነበሩበት ዘመን ማኅበራዊ ሰብአዊ ገጽታውን በማንበብ የነበረውን የጽአት ክስተት ዓቢይ ግምት በመስጠት ሁሉም ባለበት ሥፍራና ጊዜ በሕይወት አጋጣሚ ሁሉ እንዲገለገልበት ብቻ ሳይሆን በኵላዊነት መልኩ እምነቱን ተገንዝቦ እንዲኖር ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥረኛ በሚል ስያሜ የሚታወቀው የትምህርተ ክርስቶስ መጽሐፍ ደርሰው፣ ጥልቁን እምነት ይዞታውንና አንቀጹን በማስጠበቅ ግልጽ ጠንቃቃና ውጤታማ በሆነ ቀለል ባለ ቋንቋ አማካኝነት ለሁሉም ያቀረቡ ናቸው” በማለት ቅዱስ አባታችን እንዳስታወሱዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ የጴጥሮሳዊ ተልእኮአቸው ሐዋርያዊ መለያ፦ “Instaurare omnia in Christo- ሁሉንም ነገር በክርስቶስ ማደስ” የሚል እንደነበርና ሊጡርጊያ የቤተ ክርስትያን ማኅሌት በጠቅላላ የውስጥዋ መዋቅር ሁሉ ምእመናንን ወደ ጥልቅ የጸሎት ሕይወትና በቅዱሳት ሚሥጢራት ሙሉ ሲታፌ የሚመራ እንዲሆን በማድረግ የገለጡት መለያ ሲሆን፣ ሕፃናት በሰባት ዓመት እድሜያቸው የመጀመሪያ ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ በማድረግ አርቆ አሳቢነታቸው የሚመሰክር ለውጥ በቤተ ክርስትያን ያመጡ መሆናቸውም የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር ይመሰክራል።
ቅዱስ አባታችን አክለውም “ውዶቼ፦ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ፒዮስ አሥረኛ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎትም ይሁን በምንሠራበትና በምናገለግልበት በሁሉም ሥፍራ ከክርስቶስ ጋር የጠበቅ ውህደት እንዲኖረን ሁለመናችን አለ ፈረቃ ከክርስቶስ ጋር የተወሃደ እንዲሆን ይኽንን መንፈሳዊነት ዕለት በዕለት እንድናበረታው በጴጥሮሳዊ አገልግሎታቸው ላቀረቡት አስተምህሮ ማእከል ነበር” በማለት እንደገለጡዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ገልጦታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.