2012-08-22 13:09:54

33ኛው ዓለም አቀፍ“Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የጥናት ጉባኤ


ባለፈው እሁድ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊሊያ ሮማ አቅራቢያ በምተገኘው ሪሚኒ ከተማ “Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የተየሰየመው ካቶሊካዊ ማኅበርሰብ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው RealAudioMP3 ዓለም አቀፋዊ ዓወደ ጥናት በመቀጠል “የሰው ልጅ ዓይነተኛው ባህርይ ከወሰን አልቦ ጋር ተገናኝነት” በተሰየመው ጠቅላይ ርእስ ሥር የማኅበርሰቡ መሥራች ስመ ጥር ነፍሰ ኄር ክቡር አባ ልዊጂ ጁሳኒ “ሃይማኖታዊ ስሜትና ትርጉም” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት አቢይ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ጥናታዊ ሰነድ ላይ በማተኮር የዘንድሮ 33ኛው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፣ ትላትና ሃይማኖትና ነፃነት-የሃይማኖት ነፃነት በሚል ርእስ ሥር አስተምህሮ ተደርጎ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ሲገለጥ፣ በሰውና ወሰን አልቦ መካከል ያለው ግኑኝነት ላይ በማተኮር በዚህ ርእስ ሥር የሃይማኖት ነፃነትና ሃይማኖትና ነፃነት ጉዳይ በጥልቀት ተገልጦ ውይይት ተደርጎበታል።
በአውደ ጥናቱ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በረገንስቡርግ የሰጡት አስተምህሮ ላይ ማአክል በማድረግ የመጪው ተጋርጦ ዓይነቱን በመለየት የበረገንስቡርግ አስተምህሮ ወቅታዊነቱን በማመልከት ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ገጽታውን በጥልቀት ሲተነትኑ፣ የሕገ ቀኖና ሊቃውንት አቢይ ትንትና ከተሰጠበት በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ያላቸው የቲዮሎጊያ ሊቅ ኻቪየር ሎፐዝ ሰውና ወሰን አልቦ፣ “የሰው ልጅ ዓይነተኛው ባህርይ ከወሰን አልቦ ጋር ተገናኝነት” የሚለው የዓውደ ጥናቱ ማእከላዊ ርእስ ሥር አስተምህሮ እንዳቀርቡ ሲገለጥ፣ በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጥናት ሂደቱ በሪሚኒ ዓውደ ጥናት ማኅበር ሊቀ መንበር ኤሚሊያ ጓርነይሪ አማካኝነት እየተመራ መሆኑ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.