2012-08-20 13:53:18

ዝክረ አንደኛው ዓመት የማድሪድ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


በከለን ቀጥሎ በሲድነይ ከተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቀጥሎ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 16 ቀን እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በክርስቶስ ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ በተማራችሁት መሠረት በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ…” (ቆላ. 2፣ ቍ. 7) በተሰኘው ቃለ አዲስ ኪዳን ተመርቶ በማድሪድ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች RealAudioMP3 ቀን አንደኛው ዓመት መታሰቢያ ምክንያት የማድሪድ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት የምስጋና መልእክት፦ ማድሪድ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በብዙ ሚሊዮን ለሚገመተው ወጣት ልብ ወንጌላዊ ወቅት” መሆኑ በማረጋገጥ ቅዱስ አባታችን በማድሪድ ተገኝተው ለወጣት ትውልድ በሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮና ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት አማካኝነት ኵላዊት ቤት ክርስትያን ለወጣት ትውልድ አሳቢነቷ መመስከሩ አብራርተው፣ በስፐይን ምእመናንና በአገሪቱ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ስም ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ማመስገናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ትላንትና እሁድ ዝክረ አንደኛው ዓመት የማድሪድ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በስፐይን በሚገኙት በሁሉም ሰበካዎችና ቁምስናዎች ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ታስቦ፣ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እምነት የብርሃን የእውነትና የሕይወት በር መሆኑ የሚመሰከርበት በእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን አማካኝነት የሚዘጋጅ መሆኑ አስታውሰው፣ ዓለም አቀፍ የውጣቶች ቀን የሚስተናገድበት አገር ላስተናጋጁ አገር አቢይ ጸጋ ነው በማለት የእምነት አመት ምክንያትም ዝክረ አደኛው ዓመት የማድሪድ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለወንጌላዊ ተልእኮ ጅማሬዎች ማነቃቃቱንም ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.