2012-08-20 13:42:18

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለአገር ጋቦን መልእክት አስተላለፉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋቦን በሚገኘው በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ዣን ሮመዮ ፓውሎቭስኪ አማካኝነት ለጋቦን 52ኛው የነጻነት ቀን ምክንያት ለአገሪቱ ርእሰ ብሔር RealAudioMP3 አሊ ቦንጎ ኦንዲምባ የመልካም የነጻነት ቀን ምኞት መግለጫ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው ጋቦን ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1960 ዓ.ም. ነጻ የወጣችበት 52ኛው የነጻነት ቀን በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት፣ ለአገሪቱ ደስታና ሰላም ተመኝተው፣ እግዚአብሔር አገሪቱና ሕዝቧን እንዲጠብቅ ጸልየው፣ ጋቦን በዓለም አቀፍ ግኑኝነት መስክ መከባበርና ትብብር ያስቀደመ ግኑኝነት እንዲበረታ በማድረጉ ረገድ ትጠነክር ዘንድ አደራ በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.