2012-08-20 13:47:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “በመስተንግዶና በግብረ ሰናይ የእምነት ውበት ማሳወቅ”


የአርጀንቲና “ፈደራላዊ የካቶሊክ ተግባር” ከትላትና በስትያ በሉኻን ከተማ 27ኛው ጠቅላይ ጉባኤ” እያካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመስተንግዶና በግብረ ሰናይ አማካኝነት የእምነት ውበት ማሳወቅ” የተሰኘው ቋሚ ነገር ማእከል ያደረገ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ የካቶሊክ ተግባር RealAudioMP3 ዋና ዓላማው ወንጌል ማበሰር መሆኑ ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን፣ የካቶሊክ ተግባር አባል መለያ፦ “እንግዳ ተቀባይነትና ቸርነት” መሆኑ ገልጠው፣ “በዚህ መልኩ እምነት ያለው ውበት አብሳሪ ለመሆን የተጠራ ነው። ብለዋል።
የካቶሊክ ተግባር ማኅበር፦ “ህዝባዊ ኃላፊነት እና እውነተኛ የአገር አገልጋይ ዜጋ የሚያንጽ ሕዝባዊና አወንታዊ ባህል የሚያስፋፋ” መሆኑ ቅዱስነታቸው በማስታወስ፣ “የቅድስና ሕይወት ማሰልጠኛ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት መስፋፋት በዕለታዊ ሕይወት በቃልና በሕይወት በጥልቀት ወንጌልን እንዲኖር የሚያግዝ” ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ ከመላ አርጀንቲናና ከአንዳንድ የላቲን አመሪካ አገሮች የተወጣጡ 7 ሺህ አባላት የሚያሳትፈው የካቶሊክ ተግባር ጉባኤ፦ “የእምነት የጥሪና የተልእኮ በዓል መሆኑ” ቅዱስ አባታችን አብራርተው ይኽ የሚላችሁን አድርጉ፣ ተስፋ ዘሪዎችና የሕይወት አገልጋዮች” በሚል ርእስ ሥር የሚመራው ጉባኤ በሌላ መልኩም “አስፍሆተ ወንጌል በላቲን አመሪካ የሚከተለው ሥልትና ይዞታውንም ጭምር የሚወያይ” እንደሚሆንም ገልጠው፣ መልካም ጉባኤ ተመኝተው ተጋባእያኑን በጸሎታቸው እንደሚሸኙዋቸው በማረጋገጥ ሐዋርያዊ ቡራኬ እንዳስተላለፉም የገለጠው ቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በጉባኤው የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኾሴ ማሪያ አራንሰዶ፣ የማኅበራዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኾርኸ ሎዛኖ፣ የማኅበራዊ ጉዳይ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አጉስቲን ራድሪዛኒ እየተሳተፉ መሆናቸውም አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.