2012-08-20 13:34:17

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረ ለመሆኑ እሺ ማለት ይጠበቅበታል”


ትላትና በኢጣሊሊያ ሮማ አቅራቢያ በምተገኘው ሪሚኒ ከተማ “Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የተየሰየመው ካቶሊካዊ ማኅበርሰብ በየዓመቱ የሚያካሂደው ዓለም አቀፋዊ ዓወደ ጥናት በመቀጠል “የሰው ልጅ ዓይነተኛው ባህርይ ከወሰን አልቦ ጋር ተገናኝነት” በተሰየመው ጠቅላይ ርእስ ሥር RealAudioMP3 የማኅበርሰቡ መሥራች ስመ ጥር ነፍሰ ኄር ክቡር አባ ልዊጂ ጁሳኒ “ሃይማኖታዊ ስሜትና ትርጉም” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት አቢይ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ጥናታዊ ሰነድ ላይ በማተኮር የዘንድሮ 33ኛው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ትላትና በይፋ መጀመሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ ለተግባእያኑ ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረ ለመሆኑ እሺ ማለት ይጠበቅበታል” በሚል ጥልቅ ሓሳብ ላይ ያነጣጠረ ዓወደ ጥናቱን በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ላስጀመሩት ለሪሚኒ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ላምቢያሲ ባስተላለፉት መልእክት፣ “ስለ ሰው ልጅ መናገርና ወደ ወሰን አልቦ ያቀና ነው ሲባል ከፈጣሪ ጋር ያለው ግኑኝነት መሠረታዊ መሆኑ የሚገልጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረ መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው። በአሁኑ ወቅት ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረ ነው የሚለው እውነት፣ ጊዜው ያለፈበት ፈሊጥ ሆኖ ሰው በገዛ እራሱ የተፈጸመና የገዛ እራሱ እጣ ጠቢብ አድርጎ ማሰቡን በመምረጥ፣ ከእግዚእግዚአብሔር ጋር ያለው መሠረታዊ ግኑኝነት ለማግለል ብዙ ጥረት በማድረግ ላይ ቢገኝም ቅሉ፣ በተሳሳተ አኗኗርም ይሁን፣ ልቡ ወደ እግዚአብሔር የሚል ወሰን አልቦ የሚሻ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።” ቅዱስ አባታችን ይኸንን የገለጡት ሃሳብ በጥልቀት ሲያስረዱ፦ “ወደ ወሰን አልቦ ያቀና መሆኑ የሚገልጥ ባህርዩን በተለያየ መንገድ ለመኖር ጥረት ያደርጋል። በሥርዓት አልቦና በተሳሳቱ ሃይማኖቶች አማካኝነት ሲገልጠውም ይታያል። ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረ መሆኑና የእግዚአብሔር ጥገኛ መሆኑ ዳግም መገንዘብ ይኖርበታል። ይኽ የእግዚአብሔር ጥገኛ መሆኑ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ካለው ግንዛቤ ለመነጨ ለጥልቅ ኃሴት ምክንያት ይሆንለታል” ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ትላንትና የኢጣሊያ መርሔ መንግሥት ማሪዮ ሞንቲ “ወጣት ትውልድ፣ ልማትና ኤኮኖሚያዊ እድገት” ዙሪያ ሰፊ አስተምህሮ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ላምቢያሲ በመካሄድ ላይ ስላለው ዓወደ ጥናት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “ሰው ለገዛ እራሱ በቂነት የለውም፣ ግኡዛዊ ነገርም ይሁን ከሌሎች ጋር ያለው ግኑኝነት አይበቃውም፣ ርእሰ አጥጋቢነት የለውም። ስለዚህ ወሰን አልቦ እርሱም እግዚአብሔር የሚሻ ፍጥረት ነው። ፈላስፋ ኪየርከጋርድ ‘ሰው ወሰን አልቦ የተጠማ ንቃቃት መሆን ነው’ በማለት እንደሚገልጠው ዘክረው፦ “ስለዚህ እውነተኛው እርካታው እግዚአብሔር ነው። ሰው ወደ ወሰን አልቦ ያቀና አቅም በመሆኑም፣ ይኸንን መሆናዊ ባህርዩን መገንዘብ ይጠበቅበታል” ካሉ በኋላ አያይዘውም፦ “ይኽ ወሰን አልቦ የክርስትናው እምነት በኢየሱስ ናዝራዊ የተገለጠ መሆኑና በኢየሱስ አማካኝነት የምንገናኘው ፈጣሪ መሆኑ የሚያስረዳ ዓወደ ጥናት ነው” ብለዋል።
ይኽ የሪሚኒ ዓውደ ጥናት ዓቢይ ዓለም አቀፋዊ የሥነ ባህል ቀነ ቀጠሮ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ላምቢያሲ ካብራሩ በኋላ ኅብረ ሃይማኖታዊ ገጽታ ያለው መሆኑ ጠቅሰው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.