2012-08-17 14:07:53

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት የሓዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ


ዕድሚያቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሓዘን መግለጫ ቴሌግራም ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት የሓዘን መግለጫ መልእክት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ጳውሎስ በኢትዮጵያ ኦርቶዲክስ ቤተ ክርስታይንና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መካከል የጋራው ውይይት ለማረጋገጥ የሰጡት ዓቢይ አስተዋጽዖ ጠቅሰው፣ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ቫቲካን ተካሂዶ በነበረው የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በእንግድነት ተሳትፈው ያሰሙት ንግግር ቅዱስ አባታቸን በማስታወስ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት ላዘኑት ሁሉ ቅርብ በመሆን ለነፍሰ ኄር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ጳውሎስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው እንደሚጸልዩ ማረጋገጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.