2012-08-15 13:07:05

የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ለበዓል ፍልሰታ ያነቃቃቸው ጅምሮች


እንደ ተለመደው በየዓመቱ ለበዓለ ፍልሰታ ለማርያም ምክንያት የቅዱስ ኤጂዲዮ የካቶሊክ ማኅበረሰብ የተለያዩ ማኅበራዊ ምንፈሳዊና ሰብአዊ ጅምሮች ማነቃቃቱ RealAudioMP3 የማኅበሩ መግለጫ አስታወቀ።
ስደተኞች በእድሜ የገፉት በሥራ አጥነት የተጠቁት በኤኮኖሚ ድኽነት እንዲሁም በተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር ምክንያት ተገፋፍተው በሮማ ከተማ በጎዳና ለሚተዳዳሩት 1500 ድጋፍ ማቅረቡ ተገለጠ። ይኽ የጎዳና ተዳዳሪው በሚገኙበት ሥፍራ በመሄድ በተፈጸመው ግብረ ሠናይ በሮማ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን መሳተፋቸውም ከተሰጠው መግለጫ ለመረዳትም ተችለዋል።
የተለያዩ የበገ ፈቃደኞ ማኅበር አባላት ክርትስያን ምእመናን በዚህ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ ጅምሮች በመሳተፍ በዓለ ፍልሰታ ከኔ ቢጤ ጋር በሚል መርህ ሥር ሰብአዊ አገልግሎት በማቅረብ በዓሉን አብረው እንዳከበሩትም የቅዱስ ኤጂዲዮ መግልጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.