2012-08-15 13:04:17

አባ ሎምባርዲ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቫቲካን ፍርድ ቤት ዳኞች ተግባር አክባሪ”


የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ የቫቲካን የበላይ ፍርድ ቤት ወንጀል አጣሪ ዳኞች ከቫቲካን ጥብቅ የግል ሰነዶችን በስውር ምስል ግልባጭ በማስቀረት በማሾለክ የተፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ የቀድሞ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መኖሪያ ቤት RealAudioMP3 ተባባሪ ነበር ፓውሎ ጋብሪኤለ ላይ የተካሄደው የማጣራት ምርመራ መሠረት፣ የተጠያቂነት ሰነድና ሊሰጥ የሚገባው ፍርድ በማያያዝ የወንጀል አጣሪው የበላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ፒየሮ አንቶኒዮ ቦነት ያጠናቀሩት ስነድ በማደገፍ በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ለጋዜጠኞች መግለጫ በመስጠት፣ በዚሁ በተፈጸመው ወንጀል ተባባሪነት የቅድስት መንበር ዋና ጻሓፊ ቢሮ ሠራተኛ ክላውዲዮ ሻርፐለቲ በወጀሉ የተባባሪነት ተጠያቂ ነው በሚል ክስ መሠረት ለፍርድ መቅረብ አለበት የሚል ውሳኔ የታከለበት መሆኑም አስታውቀዋል።
የተካሄደው አንደኛው የወንጀል ችሎት የምርመራው ፍጻሜ እንዳልሆነ አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ የተሰጠው ውሳኔ ሁለቱ ተከሳሾች የሚመለከት ሲሆን፣ የቫቲካን የወንጀል አጣሪው የበላይ ፍርድ ቤትና የብፁዓን ካርዲላኖች ድርገት ጭምር ምርመራው እንደሚቀጥሉበት ነው ብለዋል። ስለዚህ የቀረበው የተጠያቂነት ሰነድና ሊሰጥ የሚገባው ፍርድ በማያያዝ የወንጀል አጣሪው የበላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ፒየሮ አንቶኒዮ ቦነት ያጠናቀሩት ሰነድ፣ አንድ ተጨባጭ እርምጃ መሆኑና የምርመራው ሰነድ በጽናትና በግልጽነት አለ ምንም አቋራጭና ሽፍንፍን ተጠናቅሮ የቀረበ ቢሆንም፣ ለምርመራ ሊቀርቡ የሚገባቸው የሌሎች ሰዎች ስም የሰፈረበት ሆኖም ጉዳዩ ገና መጣራት ያለበት ከመሆኑ አንጻር ታቅቦ የሚያዝ መሆኑ ነው ተመልክቶ ይገኛል። የእነዚህ ሰዎች ስም በይፋ አለ መዘርዘሩ ተገቢም ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቫቲካን ፍርድ ቤት ዳኞች ሥራ ሲያበረታቱ የፍርድ ቤቱ ሥራ ምንኛ ጽኑ ጥልቅ ከማንኛውም ዓይነት ተጽዕኖ ነጻ ሉኣላዊ መሆኑ የሚያረጋግጥ በፍርድ ቤቱ ተቋም ላይ ያላቸውን እምነት የሚገልጥ፣ ግልጽነትና ቅንነት የተሟላው ሥራ የሚያጎለብት ከመሆኑም ባሻገር፣ ለቅድስት መንበር የተለያዩ ተቋሞች ውህደት የሚያረጋግጥ ታማኝነት መተባበር ኃላፊነትን መወጣት አስፈላጊ መሆኑ የሚያመለክት ነው።
ቅዱስ አባታችን ተባባሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት ዘወትር አንድነት ላይ ያተኮረ የቤተ ክርስትያን አገልግሎታቸው ፍርያማና ወንጌላዊ እንዲሆን የአገልግሎት አንድነትን በሁሉም በቤተ ክርስትያን ተቋሞች እንዲመሰክሩ በጴጥሮሳዊ ኃላፊነታቸው የሚያሳስቡት ሐዋርያዊ ዓላማ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.