2012-08-15 13:05:43

ናይጀሪያ፦ ሌላ አዲስ ጸረ ክርስትያን ጥቃት ሊጣል እንደሚችል ያሰጋል


ትላንትና የበዓለ ፍልሰታ ለማርያም ዋዜማ በናይጀሪያ ሰሜናዊ ክልል ለሚኖረው ማኅበረ ክርስትያን የጸሎትና የተስፋ ግዜ እንደሆነለት ሲነገር፣ ባለፈው ሰኞ በአንድ ጸሎት ቤት RealAudioMP3 በተጣለው ጥቃት ሳቢያ 20 ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸው ሲታወቅ፣ የአገሪቱ መንግሥት በተከታታይ የሚጣለው ጸረ ክርስትያን ዓመጽ ለመግታትና ተጠያቂዎችንም ለፍርድ ለማቅረብ ባለ መቻሉና የሚከተለው ጸጥትና ደኅንነት የማስከበሪያ ደንብ ውጤታማ ባለ መሆኑ ምክንያት የተለያዩ በአገሪት የሚገኙት የክርስትያን ማኅበራት የናይጀሪያ ርእሰ ብሔር ጆናታን ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ጥያቄ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ታውቀዋል።
የጆስ ሊቀ ጳጳሳት የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኢግናዚዩስ ካይጋማ ወቅታዊው የናይጀሪያ ጉዳይ በማስመልከት በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ማኅበረ ክርስትያን ሌላ ጸረ ክርስትያን ጥቃት እንዳይፈጸም ይጸልያል በዚሁ መንፈስ ተሸኝቶም በናይጀሪያ ማኅበራዊ ሰላም እውን እንዲሆን በበዓለ ፍልሰታ ለማርያም ስለ ሰላም ጸልየዋል። ማኅበረ ክርስትያን በማንኛውም ወቅት ለጸሎት ለቅዳሴ ለመሳሰሉት መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች ወደ ቤተ ርክስትያን ሲሄዱ የጸጥታና የደህንነት ስጋቱ አለባቸው፣ ምክንያቱም ሁሌ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ምእመናን አብረው ለጸሎትና ለአምልኮ ሲሰበሰቡ ለሞት አደጋ ዒላማ ስለ ሚሆኑ ነው። ስለዚህ ብዙዎች መብታቸው ሆኖ እያለ ወደ ቤተ ክርስትያን ከመሄድ ሲቆጠቡ ይታያል። ውሳኔው ምክንያታዊም ቢሆንም ቅሉ በቁጥር ብዛት እጅግ ከፍ ያለው የማኅበረ ክርስትያን አባላት በእምነት ተበረታተው ወደ ቤተ ክርስትያን ሲሄድ ይታያል።
ውጥረት ፍርሃት ይታያል፣ ማንኛውም ጸረ ክርስትያን ጥቃት ክርስትያናዊ ጥሪያችንን ከመኖር አያግደንም ካሉ በኋላ፣ በናይጀሪያ የተለያዩ የክርስትያን ማኅበራት የአገሪቱ መንግሥት ጸጥታና ደህንነት ለማረጋገጥ ባለ መቻሉ ርእሰ ብሔር ጆናታን ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ እየጠየቁ ናቸው። የማኅበራቱ ጥያቄ የናይጀሪያ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ጋር በመመካከር የተደረሰ ስምምነትም አይደለም፣ ብፁዕ አቡነ ካይጋማ በበኩላቸውም ርእሰ ብሔር ከሥልጣን ይውረዱ የሚለው ጥያቄ እንደማይስማሙበት ገልጠው፣ መንግሥት ጸጥታና ደኅንነት በማስከበሩ ውሳኔ ቆራጥ መሆን ይገብዋል። ማንኛው ዓይነት ግብረ ሽበራ እንዳይከሰት በተለይ ደግሞ የቦኮ ሓራም የአሸባሪያን ኃይል ንቅናቄ ለማክሸፍ እንዲሁም በመዋዕለ ንዋይ የአሸባሪያኑ ድርጅት የሚያበረታቱ አካላትና ማኅበራትም ካሉ ለይቶ ለመቆጣጠርና ለሕግ ለማቅረብ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል። ቁጥጥሩ በማሳየሉ ረገድ ጽናት ሊኖረው ይገባል ሲሉ የሰጡን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.