2012-08-13 14:23:05

ብፁዕ አቡነ ፊሲከላ፦ “የሚሰዋ ፍቅር ምስክርነት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መንገድ ነው”


በአውስትራሊያ “እኔ በጨለማ የነገርሁአችሁን በብርሃን ተናገሩት፣ በጆሮአችሁ በሹክሹክታ የነገርሁአችሁንም በሰገነት ላይ ስበኩት (ማቴ. 20.27)” የሚል ቃለ ወንጌል ማእከል ያደረገ “ብሥራተ ቃለ እግዚአብሔር 2012” በሚል ርእስ ሥር የአውስትራሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተልእኮ ወንጌል ማኅበርና የአውስትራሊያ የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ብሔራዊ ቢሮ በመተባበር ያዘጋጁት አውደ ጥናት RealAudioMP3 በንው ሳውዝ ዋለስ ግዛት በምትገኘው በቻትስዉድ ከተማ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. መካሄዱ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ያመለክታል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ፦ “የእግዚአብሔር ፍላጎት ማፈን ድምጽ እንዳይኖረው ማድረግ ወደ ራስ መቻልነት አያደርስም፣ የሰው ልጅ በቀውስ ላይ ነው የሚገኘው ስለዚህ ክርስትናን በመነጠል የበለጠና የተሻሻለ ኅብረተሰብ ለማነጽ አይቻልም።” በተሰኘው ሃሳብ ላይ በማነጣጠር የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መሠረታዊ ዓላማውን በማቅረብ “ለመጻኢ የሚጠብቀን ተጋርጦ፣ እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ በመኖር ሁኔታ ነጻነትን የሚሻ ይኸንን ፍላጎቱ ለመኖር ይቻለው ይሆናል፣ ሆኖም በዚህ የምርጫ ጉዞ የሚያጋጥመው ሁሉ ከወዲሁ ማውቅ ይገባዋል” ካሉ በኋላ የዘመኑ ሰው አቢይ ቀውስ “መሠረታዊ ተፈላጊነት ያለውን ከመዘንጋት የመነጨ ይኽም ሰው የገዛ እራሱ ነጻነት እንዳሻው ለመኖር ለሚከተለው ስልት ቀናተኛ መሆኑ የሚገልጥ ነው። ከሰው ልጅ ሕይወት እግዚአብሔርን አግሎ መኖር ለበለጠ ዓለም መረጋግጥ ዋስትና አያሰጥም፣ ስለዚህ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ተገሎ መኖርን አይቀበሉትም፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሥራት ከማሰማት ተግባር አይቆጠቡም። ይኽ ጥሪ የሚኖረው በትዕቢትና በግትርነት በመመጻደቅ ወይንም በበላይነት መንፈስ ሳይሆን፣ በትህትና በመከባበርና በታረመ ቅን ኅሊና በመኖር ነው። እንዳሉ የገለጠው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አክሎ፣ ዛሬ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ተልእኮ በዚህ ሃሳብ ላይ የጸና በመሆኑም መላ ቤተ ክርስትያን እረኞች ካህናት ዓለማውያን ምእመናን “የነበረና ያለፈ ታሪክ ተዘክሮ የሚያሰሙ ሳይሆን፣ ያንን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ ድል በመንሳት ያበሰረው የድኅነት እቅድ ህያውነቱንና ቀጣይነቱን የሚመሰክሩ ናቸው። እንዳሉም ያመለክታል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “እምነት ማርከፍከፍ ሳይሆን በዛሬው ዓለም ሙሉ በሙሉ እምነትን መኖር እንጂ የምንከተለው ሰብአዊ ስልት አይደለም ክርስትናን የሚያድነው፣ ክርስትናን የሚያድነው ክርስቶስ ሕያው እግዚአብሔር መሆኑና እርሱ በምንኖርበት ዓለም እንዲገባ የሚል ምክንያታዊና በቃልና በሕይወት የሚኖር አዲስ እምነት ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ዘወትር በየትም ሥፍራ ወንጌልና ኢየኡስ ክርስቶስ የማበሠር ግዴታና ኃላፊነት አለባት” ያሉትን ሃሳብ ብፁዕነታቸው ጠቅሰው የክርስትናው እምነት ምስክርነት ቀዳሚነት የሚል ተጨባጭ የሆነው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ለሁሉም ለእያንዳንዱ ሰው ዘር በሁሉም ሥፍራና ግዜ ማቅረብ ማለት እንደሆነም ሲያመለክቱ፦ “የድኅነት እቅድ ለሁሉም አለ ምንም ልዩነት እውነተኛ ተስፋ ነው። ሆኖም የአስፍሆተ ወንጌል መልእክት አንድ ቢሆንም የአቀራረቡ ሥልት የተለያየ ሊሆን እንደሚችል ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ያሉትን ሃሳብ በማስመር፣ “ኅያው የባህልና የእሴቶች ሃብት በአፋፍ ላይ መተው ሳይሆን፣ በማስተላለፍ የሚኖር ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን አስፍሆተ ወንጌል በአዲስና በቀጣይነት እንደምትፍጽመው የተለያዩ ሰብአውያን መሠረታውያን ትምህርቶች የመበላለጥ ሹክቻ ሲታይባቸው፣ እንዳውም ከአንቀጸ እምነት የበለጡ ናቸው ተብለውም ቢሰበኩም ሆኖም ይህ እውነት እንዳልሆነም ታሪክ ይመሰክረዋል። በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ለሃይማኖት ለእምነት ለእግዚአብሔር ያለው ፍላጎት ዳግም የተነቃቃበት ወቅት ቢመስልም፣ ፍላጎቱን የሚመቸውን ደስ የሚያሰኘውን ጥልቅ ወዳልሆኑትን ሃይማኖቶች በመግባት ሲገልጹት ይታያል፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ይኽንን ግምት በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶን የሚጠቁም ኵላዊው እምነት የሚመሰክርና የሚያስተምር መሆን አለበት። ስለዚህ ምስክርነት ታማኝና አሳማኝ እምነት ከመኖር የሚመነጭ በእግዚአብሔር ጸጋ አማካኝነት የሚሠራ ልብን እና አመለካከትን የሚያድስ መሆን አለበት። እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.