2012-08-13 14:22:55

ብፁዕ አቡነ ፊሲከላ፦ “የሚሰዋ ፍቅር ምስክርነት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መንገድ ነው”


በአውስትራሊያ “እኔ በጨለማ የነገርሁአችሁን በብርሃን ተናገሩት፣ በጆሮአችሁ በሹክሹክታ የነገርሁአችሁንም በሰገነት ላይ ስበኩት (ማቴ. 20.27)” የሚል ቃለ ወንጌል ማእከል ያደረገ ብሥራተ ቃለ እግዚአብሔር 2012” በሚል ርእስ ሥር የአውስትራሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፣ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተልእኮ ወንጌል ማኅበርና የአውስትራሊያ የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ብሔራዊ ቢሮ RealAudioMP3 በመተባበር ያዘጋጁት አውደ ጥናት በንው ሳውዝ ዋለስ ግዛት በምትገኘው በቻትስዉድ ከተማ ትላትና እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. መጀመሩ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ያመለክታል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ የእግዚአብሔር ፍላጎት ማፈን ድምጽ እንዳይኖረው ማድረግ ወደ ራስ መቻልነት አያደርስም፣ የሰው ልጅ በቀውስ ላይ ነው የሚገኘው ስለዚህ ክርስትናን በመነጠል የበለጠና የተሻሻለ ኅብረተሰብ ለማነጽ አይቻልም።” በተሰኘው ሃሳብ ላይ በማነጣጠር የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መሠረታዊ ዓላማውን በማቅረብ “ለመጻኢ የሚጠብቀን ተጋርጦ፣ እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ በመኖር ሁኔታ ነጻነትን የሚሻ ይኸንን ፍላጎቱ ለመኖር ይቻለው ይሆናል፣ ሆኖም በዚህ የምርጫ ጉዞ የሚያጋጥመው ሁሉ ከወዲሁ ማውቅ ይገባዋል” ካሉ በኋላ የዘመኑ ሰው አቢይ ቀውስ “መሠረታዊ ተፈላጊነት ያለውን ከመዘንጋት የመነጨ ይኽም ሰው የገዛ እራሱ ነጻነት እንዳሻው ለመኖር የሚከተለው ስልት ቀናተኛ መሆኑ የሚገልጥ ነው። ከሰው ልጅ ሕይወት እግዚአብሔርን አግሎ መኖር ለበለጠ ዓለም መረጋግጥ ዋስትና አያሰጥም፣ ስለዚህ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ተገሎ መኖርን አይቀበሉትም፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሥራት ከማሰማት ተግባር አይቆጠቡም። ይኽ ጥሪ የሚኖረው በትዕቢትና በግትርነት በመመጻደቅ ወይንም በበላይነት መንፈስ ሳይሆን፣ በትህትና በመከባበርና በታረመ ቅን ኅሊና በመኖር ነው። እንዳሉ የገለጠው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ጋዜጣ አክሎ፣ ዛሬ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ተልእኮ በዚህ ሃሳብ ላይ የጸና በመሆኑም መላ ቤተ ክርስትያን እረኞች ካህናት ዓለማውያን ምእመናን የነበረና ያለፈ ታሪክ ተዘክሮ የሚያሰሙ ሳይሆን፣ ያንን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ ድል በመንሳት ያበሰረው የድኅነት እቅድ ህያውነቱንና ቀጣይነቱን የሚመሰክሩ ናቸው። እንዳሉም ያመለክታል።
ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያሉትን ሃሳብ ባቀረቡት አስተምህሮ በማስተጋባት “እምነት ማርከፍከፍ ሳይሆን በዛሬው ዓለም ሙሉ በሙሉ እምነትን መኖር እንጂ የምንከተለው ሰብአዊ ስልት አይደለም ክርስትናን የሚያድነው፣ ክርስትናን የሚያድነው ክርስቶስ ሕያው እግዚአብሔር መሆኑና በምንኖርበት ዓለም እንዲገባ የሚል ምክንያታዊና በቃልና በሕይወት የሚኖር አዲስ እምነት ነው። በማለት የክርስትናው እምነት ምስክርነት ቀዳሚነት የሚል ተጨባጭ የሆነው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ለሁሉም ለእያንዳንዱ ሰው ዘር በሁሉም ሥፍራና ግዜ ማቅረብ ማለት መሆኑ ብፁዕ አቡነ ፊዜከላ ሲያመለክቱ፦ የድኅነት እቅድ ለሁሉም አለ ምንም ልዩነት እውነተኛ ተስፋ ነው። ሆኖም የአስፍሆተ ወንጌል መልእክት አንድ ቢሆንም የአቀራረቡ ሥልት የተለያየ ሊሆን እንደሚችል ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ያሉትን ሃሳብ በማስመር፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የተሰኘው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በማሰማት የተጠቀሙበት እ.ኤ.አ. በ 1979 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ሲሆኑ፣ ይኸንን የተዘራውን ሃሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በጥልቀት በመረዳትም አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚከታተል ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲመሰረት ወስነው አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በውክልና የሚፍፈጸም ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ እንዳብራሩም ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.