2012-08-13 14:17:06

ቅድስት መንበርና የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት፣ የመንፈሳዊ ማኅበረ ደናግል በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚሰጡት አስስተዋጽዖ አቢይ መንፈሳዊ ኩራት ነው


በሳንት ልዊስ የመንፈሳዊና የገዳማት ደናግል ጠቅላይ የመሪዎች ጉባኤ ፍጻሜ ቅድስት መንበርና የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት በሰሜን አመሪካ የሚገኙት የመንፈሳዊ ደናግል ማኅበር አባላት በማኅበራዊ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና በመንፈሳዊ በጤና ጥበቃ አገልግሎት በካቶሊካዊ ሕንጸት በሚሰጡት አገልግሎት እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ከኅብረተሰብ ለተነጠሉት የአገሪቱ ዜጋ፣ ስደተኞች ዘንድ የሚሰጡት RealAudioMP3 ታሪካዊ ቀጣይ አገልግሎት ለቤተ ክርስትያን ጥልቅ ኩራትና እርካታ የሚያሰጥ መሆኑ በአገሪቱ የስአትል ሊቀ ጳጳሳትና ከደናግል ማኅበራት አለቆች ጠቅላይ ጉባኤ የሚደረገው ውይይት ለካቶሊክ አንቀጸ ሃይማኖት ቅዱስ ማኅበር ሓዋርያዊ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ፒተር ሳትራይን ገልጠው፣ የተካሄደው ጠቅላይ ጉባኤ ለማኅበሩና ለመላ ቤተ ክርስትያን አቢይ ጸጋ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕነታቸው አክለውም፣ የማኅበሩ አባላት ደናግል ለመላ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና ሕዝብ ጥቅም የሚሰጡት አስተዋጽዖ ቀጣይ መሆኑና የማኅበሩ አባላት ሊከበሩና የሁሉም ድጋፍና ምስጋና እንዲሁም የሁሉም ጸሎት ያስፈልጋቸዋል ካሉ በኋላ፣ ቅድስት መንበር በሰጠቻቸው ሐዋርያዊ ኃላፊነት መሠረትም ከደናግሉ ማኅበር ጋር በተለይ ደግሞ ከአመራሩ ምክር ቤት ጋር በመተባበር የካቶሊክ አንቀጸ እምነት የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ያመለከተው መሠረታዊ ጥያቄ ማእከል በማድረግ በጸሎትና በውይይት እንዲሁም በመከባበር መንፈስ ለተከሰተውና ሊከሰት ለሚችለው አለ መግባባት መፍትሔ እንዲያገኝ አብረው እንደሚሠሩ በማረጋገጥ፣ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የገዳማውያንና የመናንያን ጥሪና ሕይወት በማነቃቃቱ ረገድ የሚካሄደው ውይይት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርት ወይንም የደናግል ማኅበር ጉባኤ አስተዋጽዖ በማክበር በመተባበር እንደሚያገለግሉ አስታውቀዋል።
የደናግል ማኅበር የአለቆች ጉባኤ ከተካሄደው ስብሰባ ፍጻሜ ከተሰጠው መግለጫ፣ የካቶሊክ አንቀጸ እምነት ተከታታይ ቅዱስ ማኅበር የደናግሉ ማኅበር በተመለከተ የሰጠው ግምገማ ማእከል በማረግ ከተወያየ በኋላ ሕጋዊና የሕገ ወጥ ስደተኞች ጸኣት ጉዳይ፣ የውጭ አገር ዜጎች ሠራተኞች በአገሪቱ የሚገኙት የውጭ አገር ስደተኞች በመጡበት አገር የሚገኙት የቤተሰቦቻቸው አባላት ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የማስገባቱ መብት፣ ይኽም ቤተሰብ ተበታትኖ ከመኖር የሚያላቅቅ መሆኑና ስለ ቤተሰብ በተመለከቱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ርእሰ ጉዳይ፣ ብሎም እጅግ አንገብጋቢ በሆኑት ግብረ ገባዊና ስነ ምግባራዊ ጥያቄዎች በተመለከቱ አበይት ርእሶች መሠረት በማድረግ ከካቶሊክ አንቀጸ እምነት ተከታታይ ቅዱስ ማኅበር ጋር ግልጽና ገንቢ ውይይት እንደሚደረግ በማስታወቅ፣ በቅርቡ ከካቶሊክ ስርወ እምነት ተከታታይ ቅዱስ ማኅበር ወኪል ብፁዕ አቡነ ፐተር ሳርታይን ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ተመልክትዋል።
የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያለው ክብር ስለ ቲዮሎጊያ፣ ስለ ሥነ ቤተ ክርስትያን እና ስለ ገዳማዊ ሕይወት ያሰፈረው መመሪያና ትርጉም የደናግል ጉባኤ በጽናት የሚከተለውና የሚያከብረው መሆኑም በስብሰባው የፍጻሜ ሰነድ የተሰመረበት ሲሆን፣ በስብሰባው ማጠቃለያ የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ እናቴ ፓት ፋረል ወቅታዊው ዓለም የሚያቀርባቸው ተጋርጦ ለመወጣት፣ አስተንትኖ ነቢያዊ ብቃት በተካነ ድምጽ፣ ከስደተኞችና ከተናቁት ጋር መተባበር፣ አመጽ አልቦ ውሳኔ ደስተኛ ተስፋ መኖር የተሰኙት ስድስት መንገዶችን በመጠቆም፣ የተባበሩት የአመርካ መንግሥታት የሕግ መወሰኛና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ ብሎም የስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ መንግሥት ተስፈኛ ተግባር የተሰየመው እቅድ እንዲያጸድቅ ጥሪ በማቅረብ ሰውን ለክብር ሰራዥ ተግባሮች የሚዳርጉት የዘመኑ ባርነትን በመቃወም ይኸንን ጸያፍ ተግባር ማጥፋት አስፈላጊነት የሁሉም ኃላፊነት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.