2012-08-08 18:51:39

የሲርያ የፖሊቲካ ቀውስ እና ግጭት ፡


በሲርያ አለፖ ከተማ ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባለበት እየቀጠለ እና ከባድ ውግያ እየተካሄደ መሆኑ እየተነገረ ነው ።በአለፖ የአልጃዚራ ዘጋቢ እንደገለጹት የሲርያ ሰራዊት የሲርያ መንግስት ሰራዊት እና ተቃዋሚዎች አለፖ ላይ ወሳኝ ሊሆን የሚችለው ከባድ ጦርነት እያካሄዱ ነው።
የአልጃዚራ ዘጋቢ እንደሚሉት ተቃዋሚዎች አንድ የመንግስት የጦር ሚግ አውሮፕላን ጥለዋል። ሳና የተባለ የሲርያ መንግስት የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ፡የመንግስት ወታደሮች
አለፖ ውስጥ የሚገኘው ሳላሐዲን የተባል ቀበሌ ተቁጣጥረዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ሁለቱ ተፈላሚዎች አለፖ ውስጥ በሚያካሄዱት ጦርነት ከበድ የጦር መሳርያ በመጠቀማቸው በሲቪል ህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው እና ከዚህ እንዲታቀቡ አመስቲ ኢንተርናሽናል አሳስበዋል።
ጸረ ሲቪል ህዝብ የሚፈጸመው ጥቃት እንደሚሚዘገብ እና የድርጊቱ ተግባር ለፍርድ ቤት ቀርበው እንደሚቀጡ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለስልጣን ክሪስቶፍ ኮቲ መግለጫ ሰጥተዋል ።
የሲርያ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባሻር አል አሳድ የሲርያ ሁኔታ ለመቆጣጠር ካልቻሉ ዝርያቸው የአላዊት ማሕበረ ሰብ የሚኖሩበት ክልል ሊፈጥሩ ያስቡ ይሆናል ይህ አስተሳሰብ ግን በዚሁ ክልል ለዓመታት የሚሄድ ህውከት እና ብጠብጥ ሊቀሰቅስ እንደሚችል የዮርዳኖስ ንጉስ ዓብዱላህ ለcbs ተለቪጂን አገልግሎት ገልጠዋል።
ሲርያ እና ዮርዳኖስ እንደሚዋሰኑ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት የሲርያ መሪ ፕረሲዳንት ባሻር አል አሳድ ጦርነት ከመቀጠል ሌላ አማራጭ የለም የሚል ሐሳብ የተላበሱ መስለው እንደሚታይዋቸው የዮርዳኖሱ ንጉስ ዓብዱላህ በማያያዝ መናገራቸው የዜና አገልግሎቱ አመልክተዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.