2012-08-08 18:44:47

በናይጀርያ በአንድ ቤተ ክርስትያን ውስጥ በተፈጸመው ፀረ-ክርስትያን ጥቃት 19 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤


በመካከለኛው ናጀርያ ከርእሰ ከተማ አቡጃ 250 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ኦኮነ በተባለች ከተማ አቅራብያ 19 የክርስትና እምነት ተከታዮች በግፍ መገደላቸው ታውቆዋል፣
ሰዎቹ የተገደሉት በአንድ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ውስጥ ሳምንታዊ የቅዱስ መጽሐፍ ትምህርት አጠናቀው ለመውጣት በመዘጋጀት ላይ እያሉ ሁለት መሳርያ የታጠቁ ሰዎች ተኩስ ለቀው 19 ሰዎች ገድለው መሸሻቸው ከቦታ የሚደርሱ ዜናዎች ያመለከታሉ፣ ለዚሁ ጥቃት ሐላፊነት የወሰደ ግለ ሰብ ወይም ቡድን ባይኖርም ሀገሪቱ ውስጥ ፀረ ክርስትያኖች ይንቀሳቀሳል ተብሎ የሚነገርለት ቦካ ሐራም የተባለ አክራሪ የምስልምና ድርጅት ሳይሆን እንደማይቀር ተገምተዋል፣
ይሁን እና የግድያ ተግባሩ ለናይጀርያ መንግሥት እና የውጭ መንግሥታት ማስደንገጡ ተመልክተዋል፣ በሰሜናዊ ናይጀርይ በሀውሳ ክፍለ ሀገር የሚንቀሳቀሰው ቦካ ሐራም የተባለ የእስላም አክራሪ ቡድን የምዕራብ ዓለም ትምህርት እርኩስ ነው በሚል መሪ ቃል እንደሚንቀስቀስ እና በክርስትያኖች ላይ በተደጋግሚ ዓመጽ መፈጸሙ የሚታወስ ነው፣ በወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ውስጥ በተሰበሰቡት ምእመናን ዘግናኝ የግድያ ተግባር የፈጸሙ ወንጀለኞች እንዳልተያዙ እና ፖሊስ አሰሳ እያካሄደ መሆኑ ከርእሰ ከተማ አቡጃ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል፣ የብሔራዊ ፖሊስ ዋና ሃላፊ መሐመድ አቡበከር ትናትና እንደገለጡት በማእከላዊ ናይጀርያ በኮጆ ስቴት የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት እና የክርስትያን ተቋሞች 24 ሰዓታት በፖሊስ እንዲጠበቁ መመርያ ሰጥተዋል፣
አሶስየትድ ፕረስ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ባላፉት ሰባት ወራት ናይጀርያ ውስጥ 660 ሰዎች ተገድለዋል፣ እኤአ ዘመን አቈጣጠር መስከረም ወር በ2010 ዓም በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጀርያ ባውቺ በተባለች ከተማ የሚገኘው ወህኒ ቤት ውስጥ 700 እስረኞች ኀይል ተጠቅሞ ማስወጣቱ የዜና አገልግሎቱ አስታውሰዋል፣
በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በህዝብ ብዛት የላቀች ናይጀርያ ባለፉት ዓመታት የእስላም ተከታዮች በብዛት በሚኖርበት ሰሜናዊ ክፍለ ሀገር ግድያ እና ሁከት መከሰቱ ይታወቃል፣ በሰሜናዊ ናይጀርያ የሚኖር ማሕበረ ሰበ ክርስትያን ጥቃቱ እና ግድያ ሰግቶ ብበብዛት ክልሉ ለቆ ወደ ደቡብ መዘዋወሩ በአንጻሩም በደቡባዊ ናይጀርያ የሚኖር የእስላም እምነት የሚከተሉ ሰዎች ደግሞ ወደ ሰሜናዊ ናይጀርያ ሲፈልሱ መታየታቸው እሶስየትድ ፕረስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል፣ ይሁን እና
ናይጀርያ ውስጥ 160 ሚልዮን ህዝብ እንደሚኖር ይታወቃል፣
የኢጣልያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጁልዮ ተርጺ በዓለም ዙርያ በተለይ በናጀርያ በክርስትያን ማኅበረ ሰቦች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ለመግታት ኤውሮጳ እና ሀገራት አቀፍ የመከላከል ስትራተጂ መቀየስ የግድ ይላል በማለት መግለጫ ሰጥተዋል፣ በማእከላዊ ናይጀርያ በወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ውስጥ የተፈጸመው የግድያ ተግባር ግብረ ሽበራ መሆኑ እና ይህ ፍጹም መገታት ያለበት ጉዳይ እንደሆነ የኢጣልያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጁልዮ ተርጺ ሳንታጋታ በማያያዝ ገልጠዋል፣ የሃይማኖት ነፃነት እየተገታ በዝምታ ሊታለፍ የማይችል ጉዳይ ስለሆነ ናይጀርያ ውስጥ በክርስትያን ማኅበረ ሰቦች ላይ የተቃጣው ጥቃት ለመግታት በኤውሮጳ ደረጃ እንደሚመከርበትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፣ በኢጣልያ ቶሪኖ ከተማ ነዋሪ የሆኑ እና የሥነ ማኅበረ ሰብ ፕሮፈሶር እና የሃይማኖት ነጻነት ታዛቢ ተቋም አቀናባሪ ማሲሞ ኢንትሮቪኘ እንዳመለከቱት፡ ቦኮ ሐራም ተብሎ የሚጠራ የእስላም አክራሪ ቡድን የሽበራ ቡድን ከመሆኑ ባሻገር በክርስትያን ላይ ያነጣጠረ ስትራተጂ እንደሚከተል እና ሌላ መቅሰፍት ከመጨመሩ በፊት ሁነኛ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፣ የኢጣልያ መንግስት ከናይጀርያ መንግስት ጋር በመተባበር ልዩ የሕግ አስከባሪ ወታደራዊ ኃይል የሚመለመልበት ሁኔታ እንደምታፈላልግ ፕሮፈሶሩ ገልጠዋል፣ እሳቸው የሚያቀናብሩት ተቋም ከሀገሪቱ የጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተያያዘ መሆኑ ይታወቃል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.