2012-08-06 12:46:26

ብፁዕ አቡነ ቸላታ፣ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት፦ አሰቃቂ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል


የዛሬ 67 ዓመት በፊት የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት በተጣለባት በጃፓናዊት የሂሮሺማ ከተማ በሚገኘው ካቴድራል በአሰቃቂው ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ለመዘከር ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት RealAudioMP3 ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ቸላታ ያንን የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ዘግናኝ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል በማለት እንደገለጡት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ በሂሮሺማ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ቀጥሎ ከሦስት ቀናት በኋላ በናጋሳኪ በተጣለው የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ሳቢያ 250 ሺህ ዜጎች ለሞት መዳረጋቸውና የፍንዳታው ጥቃት ለቀጣይ ሰብአዊና የተፈጥሮ አካባቢ ጉዳት ምክንያት ሆኖ አሁንም አቢይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ቸላታ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት ገልጠው፣ የጃፓን ሕዝብ በደረሰበት ጥቃት ቢደናገጥም በመተባበር ኃይሉንና ሰብአዊ ሃብቱንም ጭምር በማስተባበር እርስ በእርስ በመደጋገፍ ያሳየው ፍቅር እምነትና ተስፋ ለበለጠው ዓለም ሕንጸት መሠረት መሆኑ አስታውሰው፣ ሁሉም ከፍራቻና በገዛ እራስ ተዘግቶ ከመኖር ፈተና ተላቆ የመላ ዓለም ሕዝብ አንድ ቤተ ሰብ ለመሆን የሚያበቃው የእርስ በእርስ መቀራረብ፣ መደጋገፍ ተግባር ይመሰክር ዘንድ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ልብ ዘንድ የግለኝነት የራስ ወዳድነት የገዥነትና በአመጽም ይሁን በተለያዩ ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች አማካኝነት የተፈጥሮ ሃብት ለግል የማድረጉ ዝምባሌ ወይንም ፈተና እንዳለም ዘክረው፣ ሁሉም ለሁሉም እርባና በባህሎች መንፈሳዊ ሃብት በመደገፍ ሰላም እንዲመሰክር አደራ በማለት፣ ኢየሱስ ሰላምን የሚሹ ብፁዓን ናቸው በማለት እርሱ ሰላማችን ኢየሱስ እውነተኛ ሰላማችን መሆኑ መስክሮልናልና የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንጠራም ዘንድ ኢየሱስን በመከተል የሰላም መሣሪያ ሆነን እንገኝ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕነታቸው ሂሮሺማ የሚገኘው የአቶሚክ ቦምብ ቤተ መዘክር ከጎበኙ በኋላ በከተማይቱ በተካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ መርሃ ግብር መሳተፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ካሰራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.