2012-08-06 12:44:52

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የሚሰዋው የእግዚአብሔር ፍቅር እንመስክር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. መስከረም 8 እና 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የእኛ ቢጤዎችን ለመደገፍ በተለይ ደግሞ እጅግ በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙትን የአገሪቱ ዜጎች ለመደገፍ ያቀና ምጽዋት እንዲሰበሰብ ያስተላለፈው ውሳኔ ምክንያት፣ RealAudioMP3 የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የተኖረበት ባስተልለፉት መልእክት፣ ሁሉ በዚህ የቸርነትና የልገሳ ማለትም የሚሠዋው የእግዚአብሔር ፍቅር ምስክር ሆኖ እንዲገኝ በማሳሰብ “ባለ ጸጋ ሆኖ እያለ ለእኛ ብሎ ገዛ እራሱ በማዋረድ ድኽነት ለብሶ” የወረደው ጌታ በመምሰል የሚሰዋው የእውነተኛው ፍቅር መስካሪዎች ሆነው እንዲገኙ ለሁሉም የአገሪቱ ምእመናን አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ለተናቁት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት መርጃ ታልሞ የሚሰበሰበው ምጽዋት የእውነተኛው ፍቅር መስካሪነት የሚያረጋግጥ መሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት ምልእክት ጠቅሰው፦ “የምንሰጠው ክቡር ድጋፍ፣ የተጠማውና የተራበው ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ያለው ሰብአዊ ክብር የሚመሰክር ነው” በማለት ሁሉም በዚህ በተቀደው ተግባር እንዲተባበር አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.