2012-08-06 12:39:22

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “ኢየሱስን የሚያፍቅር የሌሎችን ልብ ይማርካል”
ዓመታዊ የቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ በዓል


እ.ኤ.አ ባለፈው ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሁሉም ቅምስናዎች ጠባቂ ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ ዓመታዊ በዓል መከበሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይኸንን ቅዱስ በማስመልከት በተለያየ ወቅት በተለይ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ RealAudioMP3 በሰማያዊ ቤት የተወለደበት 150ኛው ዝክረ ዓመት ምክንያት ባወጁት የክህነት ዓመት የተለያዩ ሰፊና ጥልቅ አስተንትኖና አስተምህሮ መለገሳቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ መልካም እረኛ እግዚአብሔር የልቤ የሚለው፣ እግዚአብሔር ለቁምስና የሚለግሰው ትልቅ ሃብት መሆኑ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረቡት የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ገልጠው፣ ይኽ ቅዱስ የተከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ምናልባት ለምንኖርበት ወቅታዊው ዓለም የማይበጅ ተመስሎ ሊታይ ይችል ይሆናል፣ ሆኖም ግን የተከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ምንኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተቃጠለ መሆኑ የሚያረጋግጥ ለወቅታዊው ዓለም ትልቅ ጸጋ መሆኑ ሲያብራሩ፦ “የተከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተዋጣለት እንዲሆን ያደረገው ላበሰረው ለቀደሰውና ለኖረው፣ የክርስቶስ መንጋና እግዚአብሔርን የሚሹትን ሁሉ ለማፍቅር ላበቃው ምሥጢረ ቅዱስ ቁርባን የነበረው ጥልቅ ፍቅር ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
የፈረንሳይ የድኅረ አብዮት ባህል እግዚአብሔር ከሰው ልብ ዘንድ የሚያርቅ አሊያም የሚያስወግድ በምርምር የሚደረስ መሠረተ ምክንያት ብቻ የሚል ሥነ አመለካከት ተጽዕኖ ያየለበት ቢሆንም ቅሉ፣ ቅዱስ ኩራቶ ዳርስ የሰዎች መንፈስ በእግዚአብሔር ልብ እንዲማረክ ማድረጉና ይኽንን ለማረጋገጥ ያበቃውም የገዛ እራሱ ሰብአዊ ብቃት ሳይሆን ስለ በጎቹ ገዛ እራሱን አሳልፎ የሚሰጠው መልካም እረኛን ለመምሰል ያደረገው ጥረትና በሕይወቱ ክርስቶስን ለመምሰል ያሳየው ትጋት እንደሆነም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ነሐሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረቡት የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርቶስ አስተምህሮ ሲያብራሩ፦ ኩራቶ ዳርስ መላ ሕልውናው ትምህርተ ክርስቶስ አድርጎ ለመኖር መቻሉና፣ ሲቀድስ በመንበረ ታቦት ፊት ተንበርክኮ አስተንትኖ ሲያደርግ ምሥጢረ ንስሐ ሲሠራ ያየው ሁሉ ሐዋርያዊ ክህነት ለመገንዘብ ችለዋል። እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2010 ዓ.ም. ባቀረቡት አጠቃላይ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “ገዛ እራስ በክርስቶስ እንዲማረክ ማድረግ ለምንኖርበት ዓለም የተስፋ የእርቅና የሰላም መልእክተኛ ሆኖ ለመኖር ያበቃል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የምንኖርበት ዓለም በተለያየ መልኩ የተቀደሱ ካህናት እንደሚያስፈልጉትና የቅዱስ ካህን ጥማት እንዳለው ያረጋግጥልናል፣ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ ትሁት ቅዱስ ለተጠሙት ሁሉ ክርስቶስን ለማቅረብ የሚችል፣ ከክርስቶስ ጋር ውህደትና ኅብረት እንዲኖር ይኸንን ውህደትና ኅብረት በቃልና በሕይወት የሚያስተምር ካህን እንደሚያስፈግል ሲያስረዱ፦ “ካህን ይኸንን ለማረግ የሚችለው ከክርስቶስ ጋር ፍቅር የያዘው በእርሱ ፍቅር የተቃጠለ ሲሆን ብቻ ነው። ከክርስቶስ ጋር ፍቅር የያዘው ካህን የአሕዛብ ልብ በመንካት መሃሪ ለሆነው ለጌታ ፍቅር ክፍት እንዲሆን ያደርጋል” ሲሉ ነሐሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ባቀረቡት አጠቃላይ የእለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንዳሰመሩበት የቅድስ መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.