2012-08-03 16:14:29

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤
ዛሬ በሥርዓተ አምልኮአችን የቤተ ክርስትያን ሊቅና ሊቀ ጳጳስ የሆኑ የቅዱስ አልፎንሶ ማርያ ደ ሊግዎሪ ክብረ በዓል ይታወሳል፣ ቅዱሱ በረደንቶሪስት የሚታወቀውን የጥቀ ቅዱስ አዳኝ ማኅበር መሥራች የሆኑ፤ የትምህርተ ንባበ መለኮት ሊቃውንት እና የንስሐ አባቶች ጠበቃም ናቸው፣ ቅዱስ አልፎንሶ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ ሕዝባዊና ውድ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፣ ያኔ ጃንሰኒዝም በሚባል የተሳሳተ ትምህርት በተከሠተው በታላቁ የክርክር ግዜ ቅዱስ አልፎንሶ ስለ ምሥጢረ ንስሐ ቀለል ባለ መንገድና በግብታዊነት ባቀረቡት አንቀጸ ሃይማኖታዊ ትምህርት ታላቅ ችሎታቸውን አስመስክረዋል፣ ቅዱስ አልፎንሶ አናዣዦችን የዚህ የምሥጢረ ንስሐ ሥርዓት በሚፍጽሙበት ጊዜ፤ የተጸጸተ ልጁን ለመቀበል የማይታክት እግዚአብሔር ወደር በሌለው ዘለዓለማዊ ምሕረቱ የሚያሳየውን እጁን ዘርግቶ የመቀበል አባታዊ ደስታ እንዲያሳዩ አደራ ብለዋል፣ የዛሬው የዚህ ክብረ በዓል ማስታወስ ቅዱስ አልፎንሶ ስለ ጸሎት ያስተማሩትን የተከበረና በመንፈሳዊ ዐረቦን የተሞላውን ትምህርት ለማትኰር ዕድል ይሰጠናል፣ በ1759 ዓም ቅዱስ አልፎንሶ ራሳቸው ከሌሎች ጽሁፎች ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ብለው የመሠከሩለት “ትልቁ የጸሎት መሣርያ” የሚል መጽሓፍ ጽፈዋል፣ በዚሁ መጽሓፍ መግቢያ ላይ ጸሎትን “ድህንነትንና እርሱን ለማግኘት የሚያስፈልጉንን ጸጋዎች ለማግኘት የሚጠቅመን አስፈላጊና እርግጠኛ መሣርያ” ብለው ገልጸውታል፣ ቅዱስ አልፎንሶ ስለጸሎት የሚያስተምሩት ሁሉ በዚች ዓረፍተ ነገር ይጠቃላል፣
ጸሎት መሣርያ ነው ሲል መድረስ ያለብንን ዓላማ እንድናስታውስ ይጠራናል፣ እግዚአብሔር ሕይወትን በሙላት እንዲሰጠን ዘንድ በፍቅሩ ፈጠረን ሆኖም ግን ይህ እንደ ዓላማ መደረስ ያለበት የሕይወት ሙላት እኛ ሁላችን እንደምናውቀው በሓጢአት ምክንያት እጅግ ሩቅ ሆነዋል፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ልንቀርበው እንችላለን፣ ይህንን መሠረታዊ እውነት ማለትም የሰው ልጅ የመጥፋት አደጋን ለመግለጥና በቀላሉ ቶሎ ብለን እንድረዳው ለማድረግ ቅዱስ አልፎንሶ መሠረታዊ የሆነ ቀላል ተረትና ምሳሌ አቅርበዋል፣ ምሳሌውም “የሚጸልይ ይድናል! የማይጸልይ ግን ይኰነናል!” የሚል ነበር፣ የዚህ አስቁርቋሪ አባባሉ ትንተና ሲያቀርብ “ካለጸሎት ደህንነት አስቸጋሪ ነው! የማይቻልም ነው፣ ሆኖም ግን ከጸሎት ጋር ደህንነት እርግጠኛና ቀላል ነው” ይላል፣ እንደገናም እንዲህ ይላል “ያልጸለይን እንደሆነ ምንም ምክንያት የለንም ምክንያቱም የጸሎት ጸጋ ራሱ ከእግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የሚሰጠን ነውና .. ያልዳንን እንድሆነ ጥፋቱ የእኛ ነው ምክንያቱም አልጸለይንምና”፣ ቅዱስ አልፎንሶ ጸሎት አስፈላጊ መሣርያን ነው ሲል በእያንዳንዱ የሕወታችን ኑሮ ሁሉ በተለይም በፈተናና በአስቸጋሪ ጊዜ መጸለይ እንጂ ሌላ ምንም ማድረግ እንደማንችል ሊያስረዳን ስለፈለገ ነው፣ ስለዚህ ጌታ ሁሌ ለእና ለልጆቹ እንደሚያስብልን ልብ በማለት ዘወትር ሳናመነታ በእምነት የጌታን በር ማንኳኳት አለብንን፣ለዚህም ወደ እርሱ እንድንሮጥና የሚያስፈልገንን እንደምናገኝ እርግጠኞች በመሆን ልመናዎቻችንን በመተማመን አለፍራቻ ለማቅረብ የተጠራን ነን፣
ውዶቼ የጥያቄው አንኳር በሕይወቴ ውስጥ አስፈላጊው ምንድር ነው፧ የሚለው ነው፣ ከቅዱስ አልፎንሶ ጋር በመሆን “ጤና እና ለጤና የሚያስፈልጉ ጸጋዎች ሁሉ” ብየ እመልሳለሁ፣ በእርግጥ ቅዱስ አልፎንሶ የሚናገረው ስለ የአካል ጤንነት ብቻ ሳይሆን ስለ ኢየሱስ የሚሰጠን የነፍስ ጤንነትም ነው፣ ከሁሉም ነገር ይልቅ ነጻነት የሚሰጠንና ሰብአዊ ሙላት በመስጠን ኑⶂችንን በደስታ የሚሞላው የጌታ ኢየሱስ ከእኛ ጋር መኖር ነው የሚያስፈልገን፣ እርሱንና ጸጋውን ልንቀበለው የምንችለው በጸሎት ብቻ ነው፤ በዚህም ማንኛው ሁኔታችን ማለት አእምሮአችን በማብራት እውነተኛው በጎ ነገርን ለመለየት እንችላለን እንዲሁም ፈቃዳችንን በማጽናት የለየነውን በጎ ነገር እንድናደግ ያስችለናል፣ በኑር አችን ዘወትር መልካም ነገርን ብናውቅም ቅሉ እተግባር ላይ እንድናውለው አንችልም፣ በጸሎት ግን ፍጻሜው ላይ ልንደርስ እንችላለን፣ የጌታ ኢየሱስ ሐዋርያ ሁሌ በፈተና እንደሚገኝ ያውቃል፣ ይህንን ፈተና እንዲያሸንፍም እግዚአብሔርን በጸሎት መለመን እንዳለበት ያውቃል፣
ቅዱስ አልፎንሶ አድማሚ የሆነውን የቅዱስ ፊሊፖ ነሪ ምሳሌን ይጠቅሳል፣ቅዱስ ፊሊፖ ነሪ ጥዋት ከመኝታ ሲነሳ ጀምሮ ጌታ ሆይ! በዚህች ዕለት እጆችህን በፊሊፖ ላይ እንዲውሉ ይሁን! አለበለዚያ ፊሊፖ ይክደሃል” ብሎ ይጸልይ ነበር፣ ሁኔታውን በእውነት በማወቁ እግዚብሔር እጆቹን በእርሱ ላይ እንዲዘረጋ ይጠይቃል፣ እኛ ድካማችንን በማወቅ በእግዚብሔር ምሕረት ብዛት በመተማመን በትሕትና የእግዚአብሔር እርዳታ መጠየቅ አለብን፣ በሌላ ጥቅስ ደግሞ ቅዱስ አልፎንሶ እንዲህ ይላል፤ “እና ሁላችን ድሆች ነን የጠየቅን እንደሆነ ግን ድሆች አይደለንም፣ እኛ ድሆች የሆነንን እንደሆነ እግዚብሔር ግን ሃብታም ነው”፣ እንዲህ በማለት የቅዱስ አጎስጢኖስ ዱካ በመከተል እያንዳንዱ ክርስትያን በጎ ነገር ለማድረግ ኃይል ስለሌለው ጌታ በትሕትና እርዳታውን ለሚለምኑት እንደማይተዋቸው እርገጠኛ በመሆን ይህንን ኃይል ከእግዚአብሔር በጸሎት አማካኝነት እንዲያገኙት አለ ፍርኃት እንዲቀርቡ ጥሪ ያቀርባል፣ውዶቼ ቅ.አልፎንሶ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት መሠረታዊ መሆኑን ያሳስበናል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ግኑኝነት የሌለን እንደሆነ መሠረታዊ ነገር ይጐድልብናል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ግኑኝነት የሚደረገው በዕለታዊ የግል ጸሎታችንና ምሥጢራትን በመሳተፍ ከእርሱ ጋር በመናገር ነው፣ በዚህ መንገድ ይህ ግኑንኘት ሊያድግ ይችላል፣ የሕይወት ጉዞአችን የሚያቀናው መለኮታዊው ህልውናም በኑሮ አችን ሊያድግ ይችላል፣ ይህም ጉዞአችንን በማብራት በችግርና በአደጋ መሀከልም ቢሆን እርግጠኛና ሰላማዊ ያደርገዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.