2012-08-03 16:16:42

ወጣቶች እስከ አጽናፈ ዓለም የወንጌል ምስክሮች ይሁኑ


ይህንን ጥሪ ያቀረቡት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በዚሁ በተያዝነው ወር በሚያቀርቡት ግብረ ተል እኮ አዊ ጸሎታቸው አማካኝነት ነው፣
ጳጳሳዊ የሥርዓተ አምልኮ ክፍል እንዳሳወቀው የር.ሊ.ጳ የወርሐ ነሐሰ የሐሳብ ጸሎት በወጣቶች ላይ በተለይም እፊታችን ዓመት በ2013 ዓም በብራዚል በሪዮ ዲ ጃነሮ “እንግዲህ ወደ ዓለም ሕዝብ ሂዱ የእኔ ደቀ መዛሙርትም አድርግዋቸው” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ያተኰረ ነው፣
የጸሎቱ ይዘት “ክርቶስን ለመከተል የተጠሩ ወጣቶች ወንጌልን ከጽንፍ እስከ አጽናፈ ዓለም እንዲያስተምሩና ምስክር እንዲሆኑ ፈቃደኞች እንዲሆኑ እንጸልይ” ይላል፣
ይህ ቅዱስነታቸው የሚጸልዩለት ጥሪ ለካቶሊካውያን ወጣቶች ምን እንደሚያመለክት ለማብራራት የአገረ ጣልያን ካትሊካዊ ተግባር ማኅበር ኃላፊ ለሆነች ሊሳ ሞኒ ቢዲን የቫቲካን ረድዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ጠይቀዋቸው ሲመልሱ “ቅዱስነታቸው የሚያቀርቡት ጥሪ እያንዳንዱ ወጣት የእምነት ተመኲሮ እንዲኖረው በማሳሰብ እያንዳንዳችን ወደ እምነታችን መሠረት ገብተን ከጌታ ጋር የሚሰጡንን ግኑኝነት እንድናጣጥም ነው፤ ከጌታ ጋር የተገናኘ ሰው በተለይ ወጣት ደግሞ ለተል እኮ ዝግጁነት ያሳያል፣ ሌሎች ወጣቶችም እንደ እርሱ ጌታን እንዲያገኙና እሳቸው በግላቸው እንዳጣጣሙት ሌሎች የዓለም ወጣቶችም ጌታን እንዲያገኙ ወንጌሉን ለመስበክና ለመመስከር ይነሳሳሉ” ሲሉ የተጠቀስው የወንጌል መስበክና መመስከር ጥሪ ትርጉም አብራርተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.