2012-08-03 18:12:19

ር ሊ ቃ በነዲክት የደረሱት መጽሐፍ ለንባብ መብቃቱ ተገለጸ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የኢየሱስ ክርስቶስ ሕፃንነት ትኩረት የሰጠ ኢየሱስ ናዝራዊ መጽሐፍ በመድረስ ላይ እንደነበሩ የሚታወስ

ነው ። በሰሜናዊ ኢጣልያ ቫለ”ዳኦስታ ላይ የበጋ ዕረፍት በመከታተል ላይ የሚገኙ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ቅድስነታቸው የኢየሱስ ክርስቶስ ሕጻንነት ግዜ ያነጣጠረ መጽሐፍ ድርሰው አጠናቅቀዋል ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል ።

በሌል በኩል የቅድስት መንበር የማኅተም ክፍል ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፡ መጽሐፉ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጐመ ነው ።

በነዲክት 16ኛ የደረሱት ኢየሱስ ሕጻን ያተኰረ መጽሐፍ በእናት ቋንቋቸው በጀርመንኛ ቋንቋ እንደጻፉት እና ሶስተኛ ቅጅ መሆኑ ታውቆዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እንዳመልከቱት ብቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተደረሰው መጽሐፍ ፊታችን ወርሃ ጥቅምት ለሚጀመረው ዓመተ እምነት ለምእምነናን እና ለበጎ ፈቃድ ሰዎች ዓቢይ ስጦታ ነው ።በነዲክት 16ኛ የርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው አራተኛ Enciclica ሐዋርያዊ መልዕክት ሳይጽፉ እንደማይቀሩ አመልክተዋል።

ቅድስነታቸው ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ከተሰየሙ በ2005 ጎርጎርዮሳዊ ዝመን አቁጣጠር ሶውስት ሐዋርያዊ መልእክቶች ለዓለም ህዝብ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም ።እነሱም Deus Caritas est እግዚአብሔር ፍቅር ነው በ2005 አቁጣጣሩ ጎርጎስያዊ የቀን መቁጠርያ ነው፡ Spe salvi በተስፋ ድነናል በ007 Caritas in veritate በእውነት ላይ ፍቅር አለ በ2009 ናቸው ።

ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ዕረፍት ላይ በሚገኙበት ቦታ ስለ ጣልያን ፖሊቲካ ሁኔታ ተጠይቀው ሲመልሱ የመንግስት ምህደራ ማለት በትክክለኛ እና አግባብ ባለው መንገድ ህዝብን በፍትሕ እና ሰላም መመራት ፡ እና ደግሞ የሕብረተ ሰብ ደካማ ወገኖች መንከባከብ ነው ።

በኤኮኖሚ ቀውስ ሰበብ ለችግር የተጋለጡት ችግር ላይ ሲወድቁ እና ሕይወታቸው ራሳቸው ሲያጠፉ ይታያል ቢረዱ ኖሮ ሕይወታቸው በተረፈ ነበር ብለዋል ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ።








All the contents on this site are copyrighted ©.