2012-07-31 19:03:18

የኢየሱስ አያቶች በትውልዶች መካከል የአንድነትና የፍቅር ምሳሌ ነው


የላቲን ሥርዓተ አምልኮ የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትናንትና የቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ክብረ በዓል አስታውሰዋል፣ እነኚህ ቅዱሳን የእመቤታችን ድንግል ማርያም ወላጆች ናቸው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ስለቤተሰብ በሚያስተምሩበት ግዜ ሁሌ እነኚህን ቅዱሳን የኢየሱስ አያቶች እንደ መሆናቸው መጠን በዘመናችን በብዙ ችግር የሚገኘው ቤተ ሰብ የአያቶች ተራን ከቅዱሳን ኢያቄምና ሐና በመማር ቤተ ሰቦችን በአንድነትና በፍቅር ሊመሩ እንድሚችሉ አስተምረዋል፣
ቅዱስነታቸው የዘመናችን ምጣኔ ሃብታዊና ኅብረተሰብአዊ ሂደት እግምት ውስጥ በማግባት ከኢየሱስ አያቶች ምን መማር እንደምንችል ሲገልጹ፤ “ዛሬ የምጣኔ ሃብትና የኅብረተሰብ ለውጥ በቤተሰብ ሕይወት ብዙ ነገሮችን ለውጠዋል፣ በብዛት አያቶች የሚገኙባቸው የማኅበረሰባችን የዕድሜ ባለጠጎች ተገልለው ይገኛሉ፣ ከእነዚህ አንዳንዶቹ ለቤተሰብ ሸክም ሆነው ስለሚሰማቸው ብቻቸው ለመኖር ይፈልጋሉ፣ በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ለእነኚህ ዓይነት ሰዎች በተዘጋጁ የተገለሉ ቦታዎች ይኖራሉ፣ ስለዚህ አያቶች በቤተሰብ በቤተ ክርስያንና በማኅበራችን ቦታቸውን እንዲይዙ ይሁን፣ በተለይ በቤተሰብ አያቶች የአንድነት እና እምነትንና አብሮ የመኖር ደስታ የሚሰጥ አንድያ ፍቅር ታማኝነት ምስክር ናቸው፣ ሲሉ ተማጥነው ነበር፣ቅዱስነታቸው አንዴም በመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ የዕድሜ ባለጸጋዎችና አያቶች በማኅበራችን መገኘት ለሐዋርያዊ ግብረ ተል አኮ አስፈላጊ ለሆነው የማስተማር ሂደት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ነበር፣ በተለይ የመሠረታዊ የሕይወት ዕሴቶች ምስክሮችና መዝገብ ለሆኑ ለአያቶች መጸለይ እንዳለብን ያሳስበናል፣ የአያቶች የማስተማር ሥራ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ በይበልጥ ታላቅ ሚና የሚጫወትበት ወቅትም ወላጆች ልጆቻቸውን ለማንከባከብና ለማስተማር በቂ ጊዜ የሌላቸው እንድሆነ አያቶች በዚሁ አስፈላጊ የልጆች የማደግ ጊዜ ህልውናቸው መተኪያ የሌለበት ዕሴት ነው፣ በመላው ዓለም ያሉ አያቶችን በቅዱሳን ኢያቄምና ሃና አማላጅነት አማጥናለሁ ብለው ነበር፣







All the contents on this site are copyrighted ©.