2012-07-31 18:55:19

የር.ሊ.ጳ የነሐሴ ወር የጸሎት አሳብ


በየመታረሚያ ቤቱ የሚግኙ እስረኞች ፍትሓዊ በሆነ መንገድ እንዲታዩና ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር በዚሁ ወር የር.ሊ.ጳ የጸሎት አሳብ ነው፣
በዓለም ውስጥ ከ10 ሚልዮን የሚሆኑ እስረኞች ይገኛሉ፣ ከእነዚህ እስረኞች ከግማሽ በላይ በሶስት አገሮች ይገኛሉ፣ 24% የሚሆኑ በተባበሩት መንግሥታት አመሪካ 17% በቻይና 9% በሩስያ ይገኛሉ፣ ር.ሊ.ጳ በየዕለቱ ለእስረኞች ይጸልያሉ፣ ባለፈው ታሕሳስ ረቢብያ በሚገኘው እስር ቤት ሄደው በጐበኙበት ጊዜ በእያንዳንዱ እስረኛ የኢየሱስ ግጽታ እንደሚያዩና በመጨረሻው የፍርድ ቀን ለእስረኞች ስላደረገው አመለካከት ልንጠየቅ ነን ብለው ነበር፣
እስከ እዚህ ድረስ የመጣሁት እግዚአብሔር እያንዳንዳችሁን ወደር በሌለው ፍቅር እንድሚያፈቅራችሁና ዘወትር የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችሁን እንድነግራችሁ ነው፣ አንድያ ልጅ የሆነው ጌታ ኢየሱስ እንደእናንተ ታስሮ ነበር በችሎት ፊትም ለፍርድ ቀርቦ ነበር የከበደውን የሞት ቅጣት ፍርድም ተቀብለዋል፣ ሲሉ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ጌታ ኢየሱስም በማይገባ መንገድ መታሰሩንና መሞቱን ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.