2012-07-27 17:09:45

የሶርያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሀገሪቱ ውስጥ ሰላም እየደፈረሰ መሆኑ እና ሰላም እንዲሰፍን ጠየቁ ፡


የሶርያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት የሀገሪቱ የጦርነት ሁኔታ አስከፊ መሆኑ ይፋ መግለጫ በመስጠት የዓለም ማሕበረ ሰብ ለሀገሪቱ ህዝብ መልካም እና ሰናይ አገልግሎት ለመስጠት ከፈለገ ፡ የሶርያ መንግስት እና እሱን በመቃወም በመዋጋት ላይ ያሉ ኀይላት ለሰላማዊ ድርድር እንዲቀርቡ ማድረግ ይጠበቅበታል በማለት መግለጣቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።
በሶርያ የአለፖ ግሪክ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጂን ክለመንት ጂንባርት እንዳመለከቱት በቅርቡ ጠቅላላ ሶርያ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ብፁዓን አበው እንደሚሰበሰቡ እና ሰላም ለማስፈን የተቻቸው ጥረት ያካሄዳሉ።ሶርያ ውስጥ ካቶሊካዊት ኦርቶዶክሳዊት ፕሮተስታንት አብያተ ክርስትያናት እንዳሉ ይታወቃል።
ነገ ወርሃ ሐምለ 28 ቀን ጠቅላላ የሶርያ ክርስትያኖች ስለ ሰላም ሶርያ በጋራ ለመጸለይ እቅድ መኖሩም በሲርያ የአለፖ ግሪክ ካቶሊክ ሌ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ጂን ክለመንት ጂባርት ማስገንዘባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ ገልጠዋል።
የሶርያ ጦርነት መፍትሔ እናድያፈላልጉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓረብ ሊግ የተሰየሙት ኮፊ አናን ያቀረቡት የሰላም ሐሳብ ጦርነቱ ለመግታት ተክህሎ ቢኖረውም በሀገራት አቀፍ ማሕብረ ሰብ ድጋፍ ማጣቱ እንደሚያሳዝን የጠቀሱት አቡነ ጂን ክለመንት እንደምንም ተብሎ ህዝብን እየፈጀ ያለውን ግጭት መገታት ይጠበቅበታል ብለዋል ።
በርእሰ ከተማ ደማስቆስ ብቻ ሁለት መቶ ሺ ህዝብ መፈናቀሉ የምግም እና መድኀኒት እጥረት መከሰቱም በማያይዝ አስገንዝበዋ።
ወደ ተጓራባች ሀበራት ሊባኖስ ዮርዳኖስ ቱርክ እና ዒራቅ የሸሸ የሶርያ ህዝብ ወደ ሁለት መቶሺ መጠጋቱ ይታወቃል።ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የሶኣርያ መንግስትን እየተፋለሙ የሚገኙ ኀያላት ተቃዋሚዎች ሁሉ ያቀፈ የሽግግር መንግስቲ ለመመስረት በቀጠር ዶሀ ላይ እየተሰባሰቡ መሆናቸው ተመልክተዋል።
ዕለታዊ ጋዜጣ ሳውዲ ዓረብያ አሽረቅ አል አውሰጥ እንደዘገበው ፡ የሶርያ መንግስት ትተው ወደ ውጭ ሀገር የፈረጠጡ ሜጀር ጀነራል ማናፍ ትላስ የሶርያ መንግስት ተቃዋሚዎች ሮድ ማፕ የጉዞ ካርታ ለመቀየስ እንዲተባበሩዋቸው ሐሳብ ማቅረባቸው ከሪያድ ተነግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት የሶርያ ጦርነት ለመግታት ካልቻለ የተባበሩት መንግስታት አጠቃላይ ጉባኤ እንደሚጠሩ የዓረብ ሀገራት አስታውቀዋል።
አጠቃላይ ጉባኤው ለዲሞክራስያዊት ሶርያ የሽግግር ፖሊቲካ እንዲቀይስ እንደሚጠይቁም በተባበሩት መንግስታት የሀገራቱ አምባሳደሮች ያመለክታሉ ።
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በተለይ እስራኤል የፕረሲዳንት ባሻር አል አሳድ መንግስት ባዮሎጂካል እና ከሚካል ጦር መሳርያዎች ይጠቀማል የሚል ስጋት እንዳላቸው እና ስጋቱ ከሐቅ የራቀ አለ መሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ የፖሊቲካ ተንታኞች ያመለክታሉ ።
የእስራኤል እና የዮርዳኖስ መንግስታት ከሶርያ በሚያዋስንዋቸው ድንበሮች ላይ የጠበቀ ጥበቃ እንዲደረግ መወሰናቸው የሚታወስ ነው ።
በተለያየ ኤኮኖምያዊ እና ስትራተጂካዊ ምክንያት በፕረሲዳንት ባሻር አል አሳድ የሚመራ የሶርያ መንግስት ከስልጣኑ እንዳይገለል የሚጣበቁ መንግስታት የሩስያ ቻይና እና ኢራን እንደሆኑ ተመልክተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ጨምሮ የምዕራብ እና ዓረብ ሀገራት መንግስታት የደማስቆስ መንግስት ስልጣኑ ለህዝብ እንድያስረክብ እንደሚጠይቁ የማይዘነጋ ነው ።
ይሁን እና በዩናይትድ ስቴትስ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት የበላይ ሐላፊ ነቪ ፒለይ የሶርያ መንግስት እና ተቃዋሚ ኅይላት በአጠቃላይ የሲቪል ተቋሞች ከማጥቃት እንዲቆጠቡ አጽንኦት ሰጥተው ማሳሰባቸው ከጀንቭ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.