2012-07-24 16:05:49

አፍሪቃውያን የዕጣ ፈንታቸው ባለ ቤት መሆን አለባቸው ካርዲናል አድርየን ሳር ፡


ፊታችን ወርሃ ሕዳር ብአኅጽሮተ ቃል ሰካም በተባለ የአፍሪቃ ባና የማዳካስካር የፓፓሳት ጉባኤ በቅድስት መንበር የባህል ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የስብከተ ቅዱስ ወንጌል ማሕበር በመተባበር በታንዛንያ ርእሰ ከተማ ዳሬሰላም ላይ እምነት ባህልና እድገት የሰነኘ ጉባኤ ለማካሄድ በእቅድ መያዙ ጉባኤው ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሰነጋል የዳካር ሊቀ ጳጳሳት እና የሰካም የአፍሪቃ እና ማዳካስካር ረዳት ፕረሲዳንት ብፁዕ ካርዲናል አድርየን ሳር ስለዚሁ በዳሬሰላም እንዲከናወን የታቀደው ጉባኤ በማስመልከት አስተያየት ሲሰጡ እንዳሉት ፡ ጉባኤው አፍሪቃውያን መጻኢ ዕድላቸውን ራሳቸውን ራሳቸው እንዲቀይሱ ይዘታ ያለው ጉባኤ ነው ።

ክርስትና የአፍሪቃ ባህል ሀብት መሆኑ እና ዳሬሰላም ላይ የሚካሄደው ሲምፖስዩም ጉባኤ እዚህ ላይ ተመስርቶ ለአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በጥናት የተደገፈ ፕሮየዎች ለማቅረብ ሐሳብ እንዳለው እና የአፍሪቃ ባህል ምርኩስ ያደረገ እድገት እንዲገኝ እና በአፍሪቃውያን ገቢራዊ እንዲሆን እንደሚፈለግ ብጹዕ ካርዲናል አድርየን ሳር አስገንዝበዋል ።

የመጨረሻው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ አፍሪቃውያን ጳጳሳት ፡ አፍሪቃ ተነሺ እና ዕጣ ፈንታሽ አንግበሽ ጉዞሽ ጀምሪ በሚል መሪ ቃል መፈጸሙ በሰነጋል የዳካ ሊቀ ጳጳሳት እና የሰካም ምክትል ፕረሲዳንት ብፁዕ ካርዲናል አድርየን ሳር አስታውሰዋል።

የአፍሪቃ ካቶሊካውያን ጳጳሳት አፍሪቃ አህጉር አለማኝናውም ተጽዕኖ ኤኮኖምያዊ ዕድገት እንድታሳይ ሰላም እና ፍትህ የነገሰባት ክፍለ ዓለም ትሆን ዘንዳ እንደሚመኙም ብፁዕ ካርዲናሉ አክለው ገልጠዋል።

በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ከ50 ዓመታት በፊት ከቅኝ ግዛት ቢላቀቁም ከየውጭ ተጽዕኖ ፍጹም እንዲላቀቁ እና የኤኤኮኖሚ እና ፖሊቲካ ዕጣ ፈንታቸው ባለቤት እንዲሆኑ እንደምያስፈልግም አመልክተዋል።

የአፍሪቃ ባህል ለሁለንትናዊ እድገት ጠቃሚ እና ወሳኝ መሆኑ ለአህጉሪቱ ህዝብ በተለይ ለወጣቶች ማስረዳት እና መንገር እንዲሚያሻ ጠቅሰው አፍሪቃ ለአፍሪቃውያን በአፍሪቃውያን በሚል መሪ ቃል ህዝቡን መቀስቀስ ያስፈልጋል ብለዋል በሰነጋል የዳካ ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ ካርዲናል አድርየን ሳር ።

የአፍሪቃ መንግስታት ኣናደ ጃፓን ቻያን ህንድ ከባህላቸው የሚጣጣም ከራሳቸው የመነጨ የእድገት ስልቶች ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል የሌሎች ሀገራት እድገት እንደ አርአያ መውሰድ እንጂ እንዳለው መውሰድ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ባማለት የሰካም የአፍሪቃ እና ማዳካስካር የጳጳሳት ጉባኤ ምክትል ፕረሲዳንት እና በሰነጋል የዳካ ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ ካርዲናል አድርየን ሳር አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.