2012-07-20 16:00:56

ክርስትያናዊ እሴት ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በአሁኑ ግዜ በካስተል ጋንዶልፎ የሚገኘው የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የበጋ ዕረፍት መካን እንደሚገኙ የሚታወስ ሲሆን እዚህ ኤውሮጳ ውስጥ ወቅቱ የዕረፍት ግዜ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ፡ህዝበ ክርስትያን አካላዊ ዕረፍት ብቻ ሳይሆን የነፍስ ዕረፍትም እንድያስታውሱ አሳስበዋል።

ቅድስነታቸው ወንጌል ሉቃስ ጠቅሰው ኢየሱስ ክርስቶስ የደከማችሁ እና የተጨቁናችሁ ሁሉ ወደ ኔ ኑ ዕረፍት እሰጣችሁለሁኝ እስቲ የኔ ሸክም እናንተ ውስዱት ከኔ ትማራላችሁ እኔ ሰላማዊ እና ትሑት ነኝ ያለውን በድገም ምእመናን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ እንዲከተሉ መክረዋል።

ከአንድ ሺ ቃላት አንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል እንደሚበልጥ በነዲክት 16ኛ ገልጠዋል።

በኢየሱስ ክርስቶስ አጠገብ የነበሩ ኑ እና ሸክሜን ውሰዱት ሲላቸው ምን አስበው ይሆን ያሉት ቅድስነታቸው በዚያን ወቅት ሸክሙ ሁለት እንስሳዎች ወይም አንድ ሰው የሚሸከመው የእንጨት ሳንቃ መኖሩ አመልክተዋል።

በቅዱሳን መጻሕፍት መሠረት ሰዎች እንዲሸከሙ ከተገደዱ ባርነት ነው ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከባድ የሰው ሐጢአት የተሸከመው የሰው ልጅ ስለሚወድ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ገልጠዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እስቲ የኔ ሸክም ለናንት ውሰዱት የደከማችሁ እና የተጨቁናችሁ ወደ እኔ ኑ ታርፋላችሁ ከኔም ትማራላችሁ ሲላቸው ስያገረሙ እንዳልቀሩ በነዲክት 16ኛ አስገንዝበዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎች ሰላማዊ እና ትሁት መሆኑ ሁሉም እንደገባቸው ያአለሰለሰ ጥረት ማካሄዱ ቅድስነታቸው አያይዘው አመልክተዋል።

ክርስቶስ ነፍሶቻችሁ ዕረፍት ያገኛሉ ሲል የሰው ልጅ በስጋ እና በነፍስ የቆመ መሆኑ ለማመልከት እንደሆነም አውስተዋል በነዲክት 16ኛ ።

የእስራኤል ህዝብ ከግብጻውያን ባርነት ነፃ እንደሆነ ነፍሱ እና አካሉ ፍስሃ እና ሰላም ማግኘቱ ቅድስነታቸው አስታውሰዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ሸክም ለሐዋርያቱ እውነተኛ አርነት መኖሩም አመልክተዋል።

ሸክሜን አብረን እንሸከመው ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንተባበር የእግዚኣአብሔር ተባባሪ ሁኑ ማለት እንደሆነም ገልጠዋል።

እኔ የሚሸክመው ሸክም ጣፋጭ እና ቀላል ነው እና ተባበሩኝ ይለናል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማለት በነዲክት 16ኛ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.