2012-07-20 14:22:10

ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ ለሓዋርያዊ ዑደት በመካከለኛው አፍሪካ ረፓብሊክ


የአሕዛብ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ በመካከለኛው አፍሪቃ ረፓብሊክ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የጀመረ ሐዋርያዊ ዑደት እያካሂዱ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት። ብፁዑነታቸው በዚህ በሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ዑደት RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ለሰየሙዋችው የባንጉይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዴውዶነይ ንዛፓላይንግን የአሶንጉአ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ነስትሮ ደሲረ ኖንጎ አዚያብጋይን የበርበራቲ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ደኒስ አብገንያድዚንና የአሊንዳኦ ሐዋርያዊ መስተናብር ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ስይር ነስትሮ ያፓውፓንን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅብአተ ጵጵስና እንደሚፈጽሙ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ብፁዕነታቸው ከአገሪቱ ውሉደ ክህነት አባላት ገዳማውያን የሰበካዎችና የገዳማት ዘርአ ክህነት ተማሪዎች የዓለማውያን ምእመናን ተጠሪዎች እንዲሁም ከአገሪቱ ርእሰ ብሔር ቦዚዘ ጋር እንደሚገናኙ ገልጠዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ ትላንትና የቅዱስ ማርቆስ አቢይ ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ጎብኝተው የሕንጸት ጉዳይ ኃላፊዎች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት፣ ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች የሚሰጠው ሕንጸት መንፈሳዊና ሰብአዊ ሕንጸት ላይ ያተኮረ እንዲሆንና በሕንጸት ኃላፊዎች መካከል ውህደትና ቅን ትብብር ወሳኝ መሆኑ በማብራራት፣ በቃልና በተግባር አብነት በመሆን የዘርአ ክህነት ተማሪዎችን ጥሪ በመንከባከብ ማነጽ፣ እያንዳንዱ የዘርአ ክህነት ተማሪ ጥሪውን በሚገባ በመንከባከብ ዘርፍ እንዲገነቡና የእግዚአብሔር ጥሪ ማለትም እግዚአብሔር በሚጠራው ሕይወት ለመገኘት እንዲችሉ ገዛ እራሳቸውንም ክፍት በማድረግ፣ የመንፈሳዊ የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ሕንጸት በጥልቀት በመከታተልና በማጠናቀቅ፣ እንዲሁም በግልና በህብረት በሚደረገው ጸሎት እንዲተጉ በመምራትና በማሳሰብ እየመሩ ይኸንን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መርሃ ግብር ይከተሉ ዘንድ አደራ ብለዋል።
የዘርአ ክህነት ተማሪ ሕንጸት ለአስፍሆተ ወንጌል ዓላማ ያነጣጠረ ሆኖ፣ ለተልእኮ ወንጌል የሚያዘጋጅ መሆን አለበት። ካህን መሆን ማለት እምነትና ፍቅርን መመስከር ማለት መሆኑ ገልጠው፣ ይኸንን ምስክርነት በተልእኮ ወንጌል መሠረት የሚኖር ነው። የዘርአ ክህነት ተማሪ ቅንነት፣ ታማኝነት ለፍትህና ለእውነት ቀናተኛ ለክርስቶስ ቤተ ክርስትያን አቢይ ፍቅር ያለው፣ ፍቅሩንም የሚኖር ትሁት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ውሉዳዊ ቅርበት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ውህደት ካላቸው ብፁዕን ጳጳሳት ውሉዳዊ ቅርበት ከሌሎች ካህናትና ማኅበርሰብ ጋር የወዳጅነትና የመከባበር እንዲሁም የመተባበር ቅርበት ያለው፣ የቅዱሳት ምሥጢራትና የሊጡርጊያ በግልና በማኅበር የሚኖርና የሚደገም ጸሎት አፍቃሪ ለቅዱስት ድንግል ማርያም የላቀ አክብሮት ያለው መሆን ይጠበቅበታል ካሉ በኋላ፣ የዘርአ ክህነት አስተማሪዎች ክህነት ገዛ እራስን ካለ መቆጠብ ሙሉ በሙሉ ፍቃድህና ፍላጎትህን በሞላው ለእግዚአብሔር ፍቃድ ማስገዛት የእግዚአብሔር ፈቃድ ለማፍቅር እንዲያንጽዋቸውም በማሳሰብ፣ በመጨረሻም የፍልፍናና የቲዮሎጊያው ሕንጸት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርትና አንቀጸ ሃይማኖት ተደግፎ በጥልቀት መታነጽ ይኖርበታል፣ ስለዚህ የሥነ እውቀትና የባህል ሕንጸት እጅግ ወሳኝ ነው እንዳሉ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት በማያያዝ፣ የዘርአ ክህነት ተማሪ የሚጠየቀው መመዘኛ ሁሉ ካጠናቀቀ በኋላ ብቁ ነው ተብሎ የክህነት ማእርግ እንዲቀበል የቤተ ክርስትያን ፈቃድ እንዲሆን የሚጠይቀው አስተማሪ፣ የተሰጠው ኃላፊነት ምንኛ አቢይና ጥልቅ መሆኑ መገንዘብ ይኖርበታል። ስለዚህ ሰብአዊና መንፈሳዊ ብስለት ለክህነት ጥሪ ወሳኝ መሆኑ መቼም ቢሆን መዘንጋት እንደለበትም እንዳሉ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.