2012-07-20 14:20:28

ቅድስት መንበርና ለፈብቭሪያን (የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማኅበር)


የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማኅበር እ.ኤ.አ. ከሓምሌ 9 ቀን እስከ ሓምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ ያካሄደው ጠቅላይ ጉባኤ መሠረት ባወጣው የማጠቃለያ ሰነድ፣ ማኅበሩ ከቅድስት መንበር ጋር ሕገ ቀኖናዊ መደበኛ ውህደት እንዲኖረው የሚለው ሃሳብ በተመለከተ የሰጠበት ውሳኔ RealAudioMP3 ከቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ይፋዊ መልስ ተሰጥቶበታል።
የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ እንደሚያመለክተውም፣ ውሳኔው በፒዮስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማኅበር አባላት መካከል ለጥልቅ ጥናትና ውይይት እንዲበጅ ውስጣዊ ሰነድ ሆኖ እንደሚቀር ሲታወቅ፣ ሆኖም ቅድስት መንበር የቅዱስ ፒዮስ 10ኛ የካህናት ወንድማማችነት ማኅበር ከጳጳሳዊ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ተከታታይ ድርገት ጋር ለሚያደርገው ውይይት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርግ መሆኑ ቢያሳውቅም ቅሉ ቅድስት መንበር ከካህናት ወንድማማችነት ማኅበር የሚሰጠው የተገባ ይፋዊ የመልስ መግለጫ በመጠባበቅ ላይ እንደምትገኝ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.