2012-07-16 14:27:27

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 11 ቀን ቅዱስ በነዲክቶስ ዘ ኖርቻ RealAudioMP3 ባከበረችበት ዕለት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለበጋው ዕረፍት በሚገኙበት በካስተል ጋንዶልፎ በዳኔል ባረምቦይን የሚመራው የምዕራብ ምሥራቅ ዲቫን ኦርኬስትራ ቁጥር 6 ውህደ-ሙዚቃ እረኛ የተሰየመውና ቁጥር 5 በርን የሚያንኳኳ እጣ ዕድል በሚል ርእስ ሥር ሉድዊግ ቫን በትሆቨን የደረሳቸውው የውህደ ሙዚቃ ትእይንቶች ለቅዱስነታቸው ክብር በቀረበው ትርኢት በክብርት ባለ ቤታቸው የተሸኙት ካስተል ጋንዶልፎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ ባለው በሞሮ መናፈሻ አቀባበል የተደረገላቸው የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ መሳተፋቸውና በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና በርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖለቲኖ መካከል የተከናወነው አጭር ግኑኝነትና የተደረገላቸው የእራት ግብዣ በእውነቱ ደስ የሚያሰኝ በሁለቱ መካከል ያለው ጥቅል ግኑኝነት የሚያንጸባርቅ እንደነበር ገልጠዋል።
አባ ሎምባርዲ ርእሰ ዓንቀጹን በመቀጠል፦ ያ የሙዚቃ ኦርኬስትራ ቡድን አባላት እያንዳንዱ ሙዚቀኛ የተለያየ የሚዚቃ መሣሪያ በመምታት ከተለያየው የሙዚቃ መሣሪያ የተለያየ ድምጽ አማካኝነት የተወሀደ ጥዑም የሚዚቃ ቅኝት የሚያሰማ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ አባላቱም የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ እርሱም ከአይሁድ ከምስልምና ሃይማኖትና የክርስትናው እምነት ተከታዮች የተወጣጡ በመሆናቸውም፣ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች የሚያስተባብርና የሚያስማም መሆኑ አብራርተው፣ ሰላም ለተካነው ማኅበራዊ ሕይወት ግንባታ የሚያበረታታ መሆኑ ጠቅሰው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት ያካሄዱት የሲኖዶስ ጸጋ ለክልሉ ሕዝብና በክልሉ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ለማስረከብ እ.ኤ.አ. መስከረም ወር 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአገረ ሊባኖስ ሐዋርያዊ ዑደት ለመፈጸም መወሰናቸውና ለዚህ ሐዋርያዊ ዑደት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ገልጠው፣ በሶሪያ እንዲሁም በእስራኤልና በፍልስጥኤም መካከል ያለው ዕልባት ያጣው አለ መግባባት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚያነቃቃ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማብራራት፣ “ማሕበራዊ ሰላም የጦር መሣሪያና የዓመጽ ድምጽ ዝም በማሰኘት፣ ሁሉ በትእግሥትና በውይይት ብሎም በመግባባትና በግልና በማኅበራዊ ለውጥ አማካኝነት የሚረጋገጥ ነው። በዓለም በዚያ ኵላዊ ቋንቋ በሆነው ሙዚቃ አማካኝነት ተስፋና ሰላም እንዲዘራ” በማለት ላቀረቡት ምዕዳን ውህደ ሙዚቃ ትርኢት ተጨባጭ የተሰፋ ምስክር በመሆን መስክሮታል ካሉ በኋላ፣ አባ ሎምባርዲ ቅዱስ አባታችን በሊባኖስ ለማካሄድ ለወሰኑት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት ከወዲሁ የተዋጣለት ይሆን ዘንድ መልካሙን ሁሉ እንመኛለም በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.