2012-07-16 14:25:17

የር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 15/07/2012)
“ክርስቶስ ይመስገን የቤተ ክርስያን ተግባር ዘወትር ወደፊት እንዳለ ነው”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በፍራስካቲ ከተማ እሁድ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ሐዋርያዊ ዑደት ፈጽመው የከተማይቱ ነዋሪዎች ምእመናን ውሉደ ክህነት ገዳማውያን የከተማይቱ መስተዳድር አባላት በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ለእረፍት ወደ ሚገኙበት ካስተል ጋንደልፎ RealAudioMP3 ወዳለው ሐዋርያዊ ሕንፃ ተመልሰው እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ “የክርስቶስና የቤተ ክርስትያን ተግባር ወደ ኋላ የማይል ዘወትር የሚገሰግስና እያደገ የሚሄድ ነው” በሚል ቋሚ ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ አስተምህሮ ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ በዚህ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ኩላዊት ቤተ ክርስትያን የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ ተከታይ የንኡሳን ፍራንቸስካውያን ወንድሞች ማኅበር ጠቅላይ አለቃ ቅዱስ ቦናቨንቱራ ዘ ባኛረጆ በምታከብርበት ዕለት መሆኑ ቅዱስነታቸው በመዘከር የዕለቱ ሊጡርጊያ በዚህ ቅዱስ የቤተ ክርስትያን ልጅ መንፈሳዊነት ላይ ያተኮረ መሆኑ በመግለጥ፣ “የዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በፊት በክርስቶስ የታወጀው የመዳን እቅድ ወደ ኋላ መለስ ብሎ እንደ ታሪክ ለመዘከር የሚቻል ቢሆንም፣ መቼም ቢሆን የክርስቶስ ተልእኮ ነው፣ ስለዚህም እያደገ እንጂ ወደ ኋላ የማይል ነው” ብለዋል።
በዕለቱ ሁለተኛው ንባብ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፈሶን የጻፈው መልእክት ላይ በማተኮር ጽማሬ ሐሳቡን “የእግዚአብሔር ቡራኬ እቅድ በክርስቶስ ወደ ዓለም መምጣት አማካኝነት ለመላው ሕዝብ የወረደ ጸጋ ሆኖዋል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ይላል፣ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በእርሱ የተመረጥን ነን። በእርሱ የዳንን በእርሱና በእርሱ ወንጌል የሚያምን የመፈስ ቅዱስ ምልክት ተኑሮበታል። ይኽ የታሪክ ራእይ የሚያጠቃልል የቅዱስ ጳውሎስ ማሕሌት ቅዱስ ቦናቨንቱራ አዲስነትና የሁሉም ዘመን ኅዳሴ የሚያረጋግጥ ክርስቶስ፣ የታሪክ ማእከል መሆኑ የሚያብራራው ጥልቅ መልእክቱ በቤተ ክርስትያን እንዲሰርጽ አድርገዋል። እግዚአብሔር በክርስቶስ በሙላት ተናግረዋል፣ ሁሉንም አድለዋል፣ የማይሟጠጥ ሃብት እንደ መሆኑም መጠን፣ በመንፈስ ቅዱስም ዘወትር የሚገለጥና ተጨባጭ የሚሆን ነው” ካሉ በኋላ ቅዱስ ቦናቨንቱራ ከጻፋቸው መልእክቶች ውስጥ “የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ሕይወት እንዳፈቅር ያደረገኝ፣ ከቤተ ክርስትያን ጅማሬና ከቤተ ክርስትያን እድገት ጋር ተምሳይነት እንዳለው የሚያረጋግጥልኝ ምክንያት ነው። ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ፣ ከተለወጠ በኋላ ወንጌልን በሙላት በመኖር ተጠምዶ በተለይ ደግሞ የመስቀል ምሥጢር በመኖር አምሳያ ክርስቶስ በመሆን የተለወጠ መሆኑ ይገልጥልናል” በሚል ሃሳብ የዕለቱን አስተምህሮ አጠናቀው፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን የላቲን ሥርዓት የምተከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ቀርሜሎስ ዓመታዊ በዓል የምታከብርበት ዕለት መሆኑ ዘክረው፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በአቢይ መንፈሳዊነት የኖሩት መንፈሳዊነትም መሆኑም ካስታወሱ በኋላ፣ ሁሉንም እዛው የቅዱስነታቸውን አስተምህሮ ለማዳመጥ የተገኙትን በጠቅላላ ለመላ ሕዝበ እግዚአብሔርን የቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ቀርሜሎስ ጥበቃ ተማጽነው “ከመንፈስ ክፋት ጋር በምናደርገው ትግል ቅድስት ድንግል ማርያም ከለላ ትሁነን፣ ወደ እግዚአብሔር በሚወስደውን መንገድ ትምራን” ካሉ በኋላ ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ደግመው፣ ለሁልም ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ወደ መጡበት እንዳሰናበቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.