2012-07-16 14:29:35

በቅድስት መሬት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ


በመካከለኛው ምስራቅ የክርስትያኖች ስደት ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ምክንያት ያለው መሆኑ የገለጡት በቅድስት መሬትና በቄጵሮስ ለቅድስት መንበር ሐዋያዊ ልኡክ RealAudioMP3 ብጹዕ አቡነ አንቶንዮ ፍራንኮ፣ በአረብና በእስራኤል መካከል ያለው ችግር መፍትሔ እስካላገኘ ድረስ የመካከለኛው ምሥራቅ የክርስትና እምነት RealAudioMP3 ተከታይ ዜጎች ስደት ቀጣይ ነው እንዳሉ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስትያን ደጋፊ የግብረ ሠናይ ማኅበር አስታወቀ።
እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. እንዲሁም በ 2010 ዓ.ም. በቄጵሮስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሁለት ጊዜ ለመቀበል የታደሉት በእስራኤልና ቄጵሮስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በእየሩሳሌምና በፍልስጥኤም ክልሎች የቅድስት መንበር ወኪል ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ፍራንኮ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. መስከረም 2012 ዓ.ም. የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የተካሄደው የመካከለኛው ምስራቅ የካቶሊካዊት ቤተ ርክስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የማጠቃለያ ሰነድ በማጤን የደረሱት የድህረ ሲኖሶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በመካከለኛው ምሥራቅ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፊርማቸውን በማኖር በይፋ ለማስረከብ ያለመ መሆኑ ገልጠው፣ የቅዱስ አባታችን በመካከለኛው ምስራቅ ሐዋርያዊ ዑደት ለመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ለመፍታት ፖለቲካዊ ዝክረ ነገር የሚቀይስ ይሆናል ብሎ ማሰቡ የዋህነት እንደሆነ፣ እየሩሳሌም በሚገኘው የሐዋርያዊ ልኡክ ሕንፃ አንዳንድ የጳጳሳዊ ማኅበራት አባላትን ተቀብለው ባሰሙት ንግግር በመግለጥ፣ የክልሉ ክርስትያን ምእመናን ሰላምና እርቅ እንዲያነቃቁ የሚያሳስብና ከዚህ ጥሪም ለመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ትክክለኛና ቅን ፖሊቲካዊ መፍትሔ ለማግኘት ይቻላል እንዳሉ ለሚሰቃዩት አቢያተ ክርስትያን ተንከባካቢ የግብረ ሰናይ ማኅበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን የደረሱት የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በማኅበራዊ የቤተ ክርስትያን አንቀጸ ሃይማኖት ትምህርትና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙት የምሥራቅ ሥርዓት ተከታዮች ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስትያን እርስ በእርስ ውህደት እንዲኖራቸውና ለእርስ በእርስ ውህደት ምክንያትም ከመንበረ ጴጥርስ ጋር ያለው ውህደት ነው በሚል መሠረታዊ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ነው እንዳሉ የግብረ ሠናዩ ማኅበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.