2012-07-14 15:54:39

የሊባኖስ ፓትርያርክ በቸራ ራይ ፡


በሊባኖስ የማሮናዊት ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ በቸራ ራይ የሀገሪቱ ወቃታዊ ሁኔታ ትኩረት የሰጠ ጋዜታዊ መግለጫ መስጠታቸው ኤስያ ኒውስ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።

በዚሁ የዜና አገልግሎት ዘገባ መሰረት ፡ ጠቃላላ የሀገሪቱ የፖሊቲካ ሰዎች ከውጭ ሀገራት ትእዛዝ እና መምርያ ይቀበላሉ ፡ እንዲህ ከሆነ እማ ነፃነት የለም ማለት ነው ብለው ደህንነታችን የውስጣችን አንድነት መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል ።

አያይዘው ለሊባኖስ ህዝብ ተአማንነት ከሁሉም መቅደም ያለበት ጉዳይ መሆኑም የሊባኖስ ማሮናዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ በቸአራ ራይ አጽንኦት ሰጥተው ለጋዜጠኞች መግለጻቸው ኤስያ ኒውስ የዜና አገልግሎት አመልክተዋል።

ሊባኖስ የውጭ ሀገራት ጥገኛ በመሆንዋ ሽባ ሆናለች በማለት ፓትርያርክ በቸራ ራይ ኀይለ ቃል ሰጥተው ለሀገሪቱ እና የውጭ ጋዜጠኞች መግለፃቸው የዜና አገልግሎቱ በማያይዝ ገልጠዋል።

ሊባኖስ በዓረቡ ዓለም የመሪነት ሚና መጫወት አለባት የዓረብ ሀገራትም የጠየቁ ይኬው ነው ያሉት ፓትርያርክ በቸራ ራይ ለሀገሪቱ የፒሊቲካ ባለስልጣናት አጣላልተው መውቀሳቸው ተመልክተዋል።

ባለፈው ሳምንት የሊባኖስ ሸንጎ አባል ቡጥሮስ ሐርብ ለመግደል የተካሄደው ሙከራ አስታውሰው የፖሊቲካ ገዳዮች ተመልሰው መጥተዋል ይሄም ከውጭ ጥቅም የተሳሰረ ሀገሪቱን የሚያደናቅፍ ተግባር ስለ ሆነ መወገዝ እና መገታት ያለበት ጉዳይ እንደሆነ ፓትርያርክ በቸራ ራይ ማሳሰባቸው ተነግረዋል።

ሊባኖስ ውስጥ በየግዜው የሚፈጸሙ የፖሊቲካ ግድያዎች በየፖሊቲካ ባለስልጣናት ከለላ ስለሚያገኙ እንደሆነም ፓትርያርክ በቸራ ራይ በግልጽ አስቀምጠውታል ያለው ኤስያ ኒውስ የዜና አገልግሎት ሊባኖስ ውስጥ ፍሊስጤማውያን ሄዝብላህ ሁሉም እንደፈለጉ ብረት ታጥቀው ይዞራሉ እና ይህ መረጋጋት እና ሰላም የሚያመጣ እንዳልሆነ በተጨማሪ መግለጣቸው ዘግበዋል።

የማሮናዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ በቸራ ራይ ሁላችን ለሀገራችን ሊባኖስ ልዓላውነት እና ክብር መቆም ይጠበቅብናል ማለታቸውም ተመልክተዋል።

የሊባኖስ ታሪክ እና የሕብረተ ሰቡ አወቃቀር መልክዓ መሬት አቀማማጥ ከተረዳን እና ከተመለከትን የማንኛውም ሀገር ጠላት ለመሆን አንችልም ያሉት ፓትርያርኩ የሀገሪቱ የፖሊቲካ ሰዎች እንድያስቡበት እና ፖሊስያቸው እንድያሻሽሉ ጠይቀዋል ተብለውል ።

ሊባኖስ ለመላ ዓለም ክፍት ነች ሆኖም ለማንኛውም ሀገር አገልግሎት የቆመች ግን መሆን የላባትም ሊባኖስ ከየክልሉም ሆነ ሀገራት አቀፍ ኀይሎች ያልተሳሰረች ገለልተኛ መሆንዋ ነው የሚታወቀው ።

የሊባኖስ ዜጎች አንድነታቸው በማረጋገጥ ለሀገራቸው እና ለመንግስታቸው ታማኝ መሆን አለባቸው የሊባኖስ ህዝብ ነፃ እና ዲሞክራስያዊ ሕይወት መምራት አለበት የአምባገነን አገዛዝ አይቀበልም በማለት ፓትርያርክ በቸራ ራይ ገልጠዋል በማለት ኤስያ ኒውስ አመልክተዋል።

በየዜና አገልግሎቱ አመለካከት የማሮናዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ በቸራ ራይ ለሊባኖስ የፖሊቲካ ሰዎች ልክ ልካቸውን ነግሮዋቸዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.