2012-07-13 13:06:01

የኤውሮጳ ማእከላዊ ባንክ ቤት፦ ባንኮች የሥራ ገበያ ማሳየል


የኤውሮጳ ኤኮኖሚ ለማንቀሳቀስ እና እንዲሻሻል ለማድረግ ባንኮችና የሥራ ገበያ ማጠንከር አስፈላጊ መሆኑ የኤውሮጳ ማእከላዊ ባንክ ቤት ሲገልጥ፣ የፍራንክፈርት ተቋም በበኵሉ RealAudioMP3 የኤውሮጳ አባል አገሮች ያለባቸው እጅግ ከፍ ያለው የብርድ ጫናና ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው የሥራ አጥ ችግር ለኤውሮጳ ኤኮኖሚ አለ መሻሻል ምክንያት መሆኑ በመግለጥ፣ በኤውሮጳ የኤኮኖሚ እድገት መረጋገጥ እነዚህ የተጠቀሱት ችግሮች መፍታት ላይ ያተኮረ የኤኮኖሚ እቅድ መሠረት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ሲል፣ የኤኮኖሚው ቀውስ ባጭር መጻኢ ውስጥ ይወገዳል ለማለት የሚያዳግት መሆኑና፣ የኤኮኖኖሚ መዋቅሮችን ማደስ ባንኮች ለቤተሰብና ለኢንዳትሪዎች ድጋፍ ላይ እንዲይተኵሩ ማድረግ ነው ብሏል።
ሮማ እቅራቢያ በሚገኘው ቶር ቨርጋታ ሮማ ትረ ተብሎ በሚጠራው መንበረ ጥበብ መምህር የኤኮኖሚ ሊቅ ፕሮፈሰር ልዊጂ ፓጋነቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄድት ቃለ ምልልስ የቤት ባለ ንብረት የሚከፍለው ግብር በጀርመንም ሆነ በኢጣሊያ ከፍ እንዲል ተደርገዋል፣ ይኽ የኤኮኖሚው ፖለቲካ የቤትና ሕንፃ ግንባታ እንዲያሽቆለቅል እያደረገ ነው። በኢጣሊያ በምርት አቅርቦት ገቢ ላይ ማለትም የገበያ ግብር ክፍያ ከፍ አለ ማድረግ ለምርት አቅርቦት ኤኮኖሚ ድጋፍ ነው።
የኤውሮጳ ኤኮኖሚ ከተነከረበት ግሽበት ለማላቀቅ ባንኮች በተጨባጩ ኤኮኖሚ ላይ ማተኮር ይኖርባቸዋል፣ ይክ ደግሞ የኢንዳትሪዎችና የአገልግሎት መስጫ እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑ አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.