2012-07-13 13:04:43

የሩዋንዳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ውሳኔ


በፈቃደኝነት ጽንስ ማስወረድ የሚፈቅድ በቅርቡ በሩዋንዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና እንዲሁም በሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት በኵል የጸደቀው ሕግ “ጸረ የሕይወት RealAudioMP3 ክብር ነው” በማለት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕና ሰላም ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሰርቪላይን ንዛካምዊታ፣ ድርገቱ ከሁለት ቀናት በፊት ባካሄደው ጠቅላይ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር መግለጣቸው ከሩዋንዳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተላለፈው መግለጫ ይጠቁማል።
የጸደቀው ጸረ የሕይወት ክብር የሆነው ሕግ ገቢራዊ እንዲሆን የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ፓውል ካጋሜ ፊርማ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ርእሰ ብሔሩ የይለፍ ፍሪማ ካኖሩበት ይህ በፈቃደኝነት ጽንስ ማስወረድ የሚፈቀደው ሕግ፣ እርሱም አንዲት ሴት አለ ፈቃዷ፣ በተፈጸመባት የግብረ ሥጋ ዓመጽ ወይም አለ ፈቃዷ ተገዳ ከተዳረቸው ባለ ቤት፣ ከሁለተኛ የቤተሰብ ደረጃ ቅርበት ካለው የቤተ-ዘመድ አባል ከሆነው የጸነሰች ሴት፣ ለገዛ እራስያ ሕይወት ወይንም ለተጸነሰው ሕጻን ሕይወት አደጋ ነው ከተባለ የተረገዘው ጽንስ ማስወረድ መብቷ ነው የሚለው ውሳኔ፣ ቤተ ክርስትያን በማውገዝ፣ ጸረ ሕይወት ባህል በጸረ ሕይወት ሳይሆ በሕይወት ባህል ብቻ ነው ሙሉ መልስ ለመስጠት የሚቻለው፣ የአገሪቱ ማኅበረ ክርስትያን ቀደብ ብሎ ይሕ ጽንስ ማስወረድ የሚፍቀደውም የሕግ ንፍድ የተቃወመውም ሲሆን፣ የሩዋንዳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሕይወት፣ የሰላም የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ባህል ለማነቃቃት “የሩዋንዳ የሰላም እቅድ” በሚል መጠሪያ አንድ እንቅስቃሴ ማቋቋሙ ብፁዕ አቡነ ንዛካምዊታ እንደገለጡም የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.