2012-07-11 12:56:54

የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን ጸዓት


ከባግድሃድ በስተ ሰሜን 400 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በሞሱል ክልል ይኖሩ ከነበሩት የኢራቅ ክርስትያን ማኅበርሰብ አባላት ውስጥ ባለፉት የመጨረሻ ወሮች ብቻ RealAudioMP3 5 ሺህ የሚገመቱት ክርስትያን የቤተሰብ አባላት ክልሉን ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸው ሲገለጥ፣ በሞሱል ያለው ሁኔታ ምንም’ኳ RealAudioMP3 የኢራቅ መራኄ መንግሥት ኑሪ አል ማሊኪ የኢራቅ የመከላከያ ኃይል አባላት ያካተተ የጸጥታና ደህንነት አስከባሪ ውሳኔ እግብር ላይ እየዋለ ቢሆንም ቅሉ አሁንም ውጥረት የሚታይበት ሆኖ ለሕይወት ደህንነት አስጊ አመጽ እንዳለ ይነገራል።
በኢራቅ ያለው የማኅበረ ክርስትያን ሁኔታ በተመለከተ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ለተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ መልስ የሰጡት የባግድሃድ ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሽለሞን ዋርዱኒ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ሁኔታ ለጸጥታና ለደህንነት አስጊ ነው። በኢራቅ በመንግሥት በተለያዩ የፖለቲካ ሰልፎችና በተለያዩ ሃይማኖቶች በአገሪቱ ሁኔታ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያስከትሉት ጥያቄዎች ይታያሉ፣ ስለዚህ በኢራቅ ያለው ሁኔታ ለኢራቃውያን አስጊ ከሆነ፣ ለአገሪቱ ውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል ምንኛ አስጊ መሆኑ ለመገመቱ አያዳግትም፣ ከሞሱል ከኢራቅ ሴሜናዊ ክፍል ከባግዳድ ክርስትያን የአገሪቱ ዜጎች ስደት ይታያል፣ ምክንያቱ የሰላም የጸጥታና የደህንነት ለሥራ ዕድል ዋስትና የሚያሰጥ ምልክት አይታይም፣ ብዙ ቃል ተገብተዋል ሆኖም ግን ቃል እንጂ ተግባር ሳይሆን ይቀራል።
የአገር ጥቅም ማእከል ያደረገ እርቅና ሰላም ሳይሆን፣ በአገሪቱ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ከፍተኛው የብዙኃን ጥያቄ እንዲሁም ጥቂቱ የውሁዳን የአገሪቱ ኅብረተሰብ ክፍል ጥያቄ ማእከል ያደረገ በመሆኑ፣ ማኅበራዊ ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት አወንታዊ ውጤት አይኖረውም። በሌላው ረገድም አልፎ አልፎ በኢራቃውያን ማኅበረ ክርስትያን ዘንድ ውህደት የእርስ በእርስ መደጋገፍ ፍላጎትና ተግባር መጓደል ይታያል። ስለዚህ የአገሪቱ ማኅበረ ክርስትያን የተጋረጠበት መሰናክል ለማሸነፍ የገዛ እራሱ ውህደት ማጠናከር ይኖርበታል። ምክንያቱ ውህደት ኃይል ነውና።
ብዙዎች ወደ ቱርክ ወደ ዮርዳኖስ፣ ቢሰደዱም እዛው እንዲቆዩ የሚፈቅድላቸው ደንብ ባለ መኖሩ ወደ መጡበት ሲሸኙ ይታያል፣ ብዙዎች ወደ ሊባኖስ ተሰደዋል። ወደ አንድ አገር መሰደድ ሳይሆን ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሰደድ የሚታይበት ለቀጣይ ስደት አደጋ ተጋልጠው ይገኛሉ። ለኢራቅ ሰላም ያቀና ሳይሆን የተለያዩ አገሮች የገዛ እራሳቸው ጥቅም ላይ በማተኮር ይኸንን ጥቅማቸውን ማእከል ያደረገ ለኢራቅ ሰላም መረጋገጥ የሚከተሉት መርሃ ግብር የገዛ እራሳቸው ጥቅም ዋስትና የሚያሰጥ እንጂ ለኢራቅና ለኢራቃውያን ፍትህ እርቅና ሰላም የሚበጅ አይደለም፣ ይኽ ደግሞ የሚታይ የኢራቅ ወቅታዊው ሁኔታ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.