2012-07-11 13:00:00

የመላ አፍሪካና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ


እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ህዳር ወር በታንዛኒያ ርእሰ ከተማ ዳር ኤስ ሳላም ባህልና እድገት ዙሪያ የሚወያይ የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ከጳጳሳዊ RealAudioMP3 የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ባህልና ልማት ጉዳይ የሚከታተል በአፍሪካና የአፍሪካ የተፈጥሮ ጸጋና የክፍለ አለሚቷ ተጋርጦ በተሰኘው አቀራረብ ባህልናና ልማትን ለማጤን የሚያግዝ ቋሚ ሸንጎ ለማቋቋም አልሞ የተዘጋጀ ጉባኤ አደሚካሄድ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ለዚህ ሊካሄድ ተወስኖ ላለው ጉባኤ ማዘጋጃም በአቡጃን በአይቨርይ ኮስት ከመላ አፍሪካና ማሳጋስካር የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር የሴኔጋል ርእሰ ከተማ ዳካር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ተዮዶረ አድሪየን ሳርና በባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ባርተለምይ አዱኮኑ እንዲመራ የተመለመለው የዚህ በህዳር ወር ሊካሄድ ለታቀደው ስብሰባ ያመራር ኮሚቴ የሁለት ቀናት ስብሰባ ማካሄዱ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ የህዳር ወር ጉባኤ የመላ አፍሪካና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶችን የሚወክሉ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን በተለያዩ የባህልና የልማት ዘርፍ ተሰማርተው የሚያገለግሉ ዓለማውያን ምእመናን የሚገኙባቸው በጠቅላላ 60 ተጋባእያን እንደሚሳተፉም ከወዲሁ የተወጠነው መርሃ ግብር መሠረት በማድረግ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.