2012-07-11 12:52:53

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ


በብራዚል የሪዮ ልኂቅ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኤውጀኒዮ ደ አራውዦ ሳለስ በ91 ዓመት ዕድሚያቸው ከትላትና በስትያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት የቴሌግራም የሐዘን መግለጫ መልእክት፦ RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ደ አራኡዦ ሳለስ በሕዝቦች መካከል የእውነት መንገድ በፍቅርና ማኅበረሰብን በተለይ ደግሞ እጅግ ለተጎሳቆሉትና ባልተደላደለ ኑሮ ለሚተዳደሩት ሁሉ እውነተኛ የወንጌል መስካሪ በመሆን ያገለገሉ ‘የጳጳሳዊ ተልእኮአቸው ልግስናና መሥዋዕነት በሚል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል በሚያነቃቃ መሪ ቃል ሥር እንዲመራ ያደረጉ ትጉና ቀናተኛ እረኛና ለመላ የብራዚል ኅብረተሰብ ጽኑና ለሐዋርያዊ መንበር ታማኝነት አብነት ነበሩ” በማለት እንደገለጧዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ ካዲናል ደ አራውዦ ሳለስ እ.ኤ.አ. በ1920 ዓ.ም. በብራዚል በሪዮ ግራንደ ዶ ኖርተ ግዛት በሚገኘው በካይኮ ሰበካ ሥር በምትተዳደረው አካሪ ከተማ ተወልደው፣ እ.ኤ.አ ህዳር 21 ቀን 1943 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት ተቀብለው፣ በነበራቸው የቲዮሎጊያ ሊቅነት በተወለዱበት ሰበካ የዘረአ ክህነት ተማሪዎች አበ ነፍስ፣ የኤኮኖሚ ጉዳይ ኃላፊና የካቶሊክ መንበረ ጥበብ መምህር በመሆን ያገለገሉ፣ በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12 ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. ሰነ 1 ቀን 1954 ዓ.ም. ቅብአተ ጵጵስና ተፈጽሞላቸው የቲቢካ ሥዩም ጳጳስና የናታል ተባብሪ ጳጳስ ሆነው ያገለገሉ፣ ለገጠር ክልል ነዋሪዎች የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎት በማቅረብ ያነሳሱት የፍቅር ሥራ በብራዚል ሰሜናዊ ምሥራቅ ክልል ተስፋፍቶ፣ መሃይምነት ለማጥፋት ለሕዝቡ መሠረታዊ ትምህርት አቅርቦት መርሃ ግብር በማረጋገጥ፣ ትምህርት ለሁሉም በሚል የሕንጸት አገልግሎት ላይ ያተኮረ የራዲዮ ጣቢያ ሥርጭት ያስጀመሩ፣ እ.ኤ.አ. በ 1964 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል አልቫሮ ዳ ሲልቫ ጤና መታወክ ምክንያት የሳው ሳልቫዶር ዳ ባሂያ ሐዋርያዊ መሥተዳድር እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 1968 ዓ.ም. ሢመተ ሊቀ ጳጳስና ተቀብለው በሰብአዊና መንፈሳዊ ሕንጸት ዘርፍ በማተኮር የተለያዩ ተደናቂ ጅምሮችን በማነቃቃት ሕዝብንና ቤተ ክርስትያንን ያገለገሉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ የዓለማውያን ምእመና ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ላይ ያተኮረና የኃሴትና ተስፋ ውሳኔ አርቃቂ ድርገቶች አባል በመሆን አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ፣ እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ውሳኔ መሠረት ካርዲላል እንዲሆኑ ተሹመው ከመጋቢት 13 ቀን 1971 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. የሳው ሳባስቲያው ዶ ሪዮ ደ ጃነይሮ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው፣ እ.ኤ.አ. ከህዳር 16 ቀን እስከ ታህሳስ 12 ቀን 1997 ዓ.ም. ለመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ልኡክ ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉ መሆናቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.