2012-07-11 12:54:53

ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክብር የውሁድ ሙዚቃ ትእይንት


ዛሬ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከቀትር በኋላ 12 ሰዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለበጋው ዕረፍት በሚገኙበት በካስተል ጋንዶልፎ በዳኔል ባረምቦይም የሚመራው የምዕራብ ምስራቅ ዲቫን ኦርኬስትራ ቁጥር 6 ውህደ-ሙዚቃ እረኛ የተሰየመውና ውህደ-ሚዚቃ ቁጥር 5 በርን የሚያንኳኳ እጣ ዕድል በሚል RealAudioMP3 ርእስ ሥር ሉድዊግ ቫን በትሆቨን የደረሰው የውህደ ሙዚቃ ትእይንት ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ክብር እንደሚቀርብ ሲገለጥ፣ በዚህ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሚቀርበው የውህደ ሙዚቃ ትእይንት ካስተል ጋንዶልፎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ ባለው በሞሮ መናፈሻ በቅዱስነታቸው አቀባበል የሚደርግላቸው የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ እንደሚሳተፉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ አክሎ በክብርት ባለ ቤታቸው ወይዘሮ ክሊዮ ቢቶኒ ለሚሸኙት ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የእራት ግብዣ እንደሚቃርቡላቸውም አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.