2012-07-09 13:43:45

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ሕያው ትውስት”።


ሁሌ እንደ ተለመደው በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ “ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ሕያው ትውስት” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ RealAudioMP3 የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. በሲስቲና ጸሎት ቤተ ባሳረጉት ቀዳሜ መሥዋዕተ ቅዳሴ “ሁለተኛው የቫቲካን ጉብኤ ውሳኔዎች እግብር ላይ ለማዋል በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የተጀመረው ንቁ ጥረት ቀጣይነቱ ለማረጋገጥ ያለው ፍላጎት ዳግም ለማጽናት እወዳለሁ” በማለት የገለጡት ሃሳብ፣ ቅዱስ አባታችን የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሕያው ምስክርና ለቤተ ክርስትያ ቀጣይነትና አንድነት ምልክት ናቸው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ነሚ በሚገኘው የመለኮታዊ ቃል ልኡካነ ወንጌል ማኅበር ያካሄዱት ጥብቅና ግላዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ እ.ኤ.አ. በ 1965 ዓ.ም. ወጣት ካህን የቲዮሎጊያ ሊቅ በአማካሪነት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ ሮማ በመጡበት ወቅት በተለይ ደግሞ አድ ጀንተስ የተሰየመው የጉባኤው አንዱ ውሳኔ አጠናቅሮ ለማርቀቅ የተስተንገዱበት ቤት መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በመጥቀስ፣ ባለፉት ቀናት የቅድስ መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ፣ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ወጣት ብፁዕ አቡነ ዎይትይላ ፍስሃና ተስፋ የተሰየመው የቅዱስ ጉባኤው አንዱ ውሳኔ ለማርቀቅ በተካሄደው ጥናታዊ ጉባኤ በመሳተፍ “ምሥጢረ ትስብእት ለሰው ዘር ምሥጢር እውነተኛው ብርሃን መግለጫ ነው” የሚለው ሃሳብ የተረጋገጠበት ነበር በማለት በቅርቡ አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ከተሳተፉት ጠቅላላ የጉባኤ አበውና ተሳታፍያን ሊቃውንት ውስጥ ወደ ሰላሳ የሚገመቱ ብቻ በሕይወት እንዳሉና የነዚህ የጉባኤው አበው ምስክርነት፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወቅታዊነቱ የሚያረጋገጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ በጉባኤው ላልተሳተፉና ጉባኤውን በታሪክ የሚያውቁት ወጣቶች የእምነት ተስፋ የሚያነቃቃ ነው በማለት የገለጡት ሃሳብ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በመጥቀስ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት እፊታችን ጥቅምት 2012 ዓ.ም. በይፋ የሚከበር መሆኑም በማስታወስም እ.ኤ.አ. ታሕሳስ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን አበይት ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት ባሰሙት ስልጣናዊ ንግግር፣ “ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላጸናት ቤተ ክርስትያን ቀጣይነት በሕዳሴ የሚያረጋግጥ፣ እርሱም በጊዜና በሥፍራ እድገቱን የሚመሰክር ዘወትር በጉዞ ላለው ብቸኛው ለእግዚአብሔር ሕዝብ መግለጫ ነች” በማለት በገለጡት ሃሳብ አባ ሎምባርዲ ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.