2012-07-09 13:40:06

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በመለኮታዊ ቃል ልኡካነ ወንጌል ገዳም ለሐዋርያዊ ጉብኝት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቀደም ተብሎ በቫቲካን ረዲዮ እንደተገለጠው ለበጋው ዕረፍት እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምረው ሮማ አቅራቢያ በካተል ጋንዶልፎ ባለው ሐዋርያዊ ሕንፃ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚህ የበጋው ዕረፍት ወቅት እሁድ እኩለ ቀን በይፋ ከሚመሩት ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር RealAudioMP3 በስተቀረ ጠቅላላ ሕዝባዊ መርሃ ግብሮች የበጋው ዕረፍት ሐምሌ ወር ፍጻኤ ድረስ ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንደማያከናወኑ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. በ 1965 ዓ.ም. በተካሄደው በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለመሳተፍ በነበራቸው የቲዮሎጊያ ሊቅነት መሠረት የዛሬ 50 ዓመት በፊት በመሳተፍ በዚያኑ ወቅት በዚህ ካስተል ጋንዶልፎ ክልል በነሚ ከተማ በሚገኘው የመለኮታዊ ቃል ልኡካነ ወንጌል ማኅበር ባለው ገዳም መስተንግዶ ተደርጎላቸው እንደነበር በማስታወስ፣ ዛሬ ጧት ለአጭርና ለጥብቅ ግላዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወደዚያው የመንፈሳዊ ማኅበር ቤት °Ad Gentes - ወደ አሕዛብ” በተሰየመው ማእከል እንደሄዱ ያመለክታል።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ወደ አሕዛብ በሚል አንዱ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ ርእስ ወደ ተሰጠው የመለኮታዊ ቃል ልኡካነ ወንጌል ማእከል ስላደረጉት ጥብቅና ግላዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት የመለኮታዊ ቃል ልኡካነ ወንጌል መንፈሳዊ ማኅበር ጠቅላይ ወኪል አባ ጃንካርሎ ጂራርዲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዚህ መንፈሳዊ ማኅበር ጠቅላይ አለቃ አባ አንቶኒዮ ፐርኒያ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ተላልፎ በማኅበሩ አባላት ውሉዳዊ መንፈስ በተካነው የሞቀ አቀባበል ተድርጎላቸው እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 29 ቀን እስከ ሚያዝያ 3 ቀን 1965 ዓ.ም. ከአራት ብፁዓን ጳጳሳት አምስት የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ጋር በመሆን የመጨረሻው ወደ አሕዛብ የተሰኘው ሁለተኛው የቫቲካን ጉብኤ አንዱ ውሳኔ የሆነው የመጨረሻው ሃሳቡን አጠናቅሮ ለማቅረብ በዚያ የልኡካን ወንጌል ማኅበር ቤት መስተንግዶ ተደርጎላቸው የኖሩትን ሕይወት የሚያስታውስ መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ የመለኮታዊ ቃል ልኡካነ ወንጌል ማሕበር ወደ አሕዛብ በተሰኘው ማእከል ለማሕበሩ ጠቅላይ ጉባኤ ከ 65 አገሮች የተወጣጡ 150 ልኡካን የማኅበሩ አባላት የሚገኙም ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባካሄዱት ጥብቅና ግላዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በመሳተፋቸውም ለማኅበሩና ወደ አሕዛብ የተሰኘው ውሳኔ የሚያስታውስ አቢይ ጸጋ ነው ካሉ በኋላ በዚህ አጋጣሚም በአምስቱ ክፍል ዓለም የሚያገለግሉ የማኅበሩ አባላት 6.100 እንዳሉም ገልጠው ለመላው ለማኅበሩ አባላት ልዩ ቡራኬ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.