2012-07-06 13:29:03

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ስለ ልባም ፈጣሪ፦ የቁስ አካል አናሥርና የህልዎተ እግዚአብሔር ፍለጋ


ከትላትና በስትያ ጀነቭ የሚገኘው የመላ ኤውሮጳ የኑክልየር ተመራማሪ ድርጅት ወይም የአውሮጳው የፊዚክስ ምርምር ማእከል ለነገሮች ሁሉ መጽናት ምንጭ የሆነው ቀዳሜ ወይንም የቁስ አካል አናሥር ነው የተባለው ቀዳሜ ቅንጣት ለይተው ለማግኘት መቻላቸው የተሰጠው መግለጫ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አቢይና አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ የብዙ የምርምር ተቋሞችና የምሁራን የሊቃውንት ትኵረት እያሳበ መሆኑ RealAudioMP3 ለማወቅ ሲቻል፣ ይኽ የቁስ አክል አናሥር የሆነው ቅንጣት በሌላ አገላለጥ የእግዚአብሔር ቅንጣት የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ያለው ለሥነ ፍጥረት ጥናት፣ የተፈጥሮ መጽናት የሁሉም መነሻና ፍጻሜ የሕይወት ትርጉም ለተሰኙት ጥያቄዎች አዲስ ምዕራፍ የከተፈ ግኝት ሊሆን እንደሚችል ይነገርለታል።
83 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የታላቅዋ ብሪጣንያ ተወላጅ ፐተር ሂግስ ለኢቁስ አካልነት ካልሆነ በስተቀረ ለለቁስ አካል ‘ነገሮች’ ሁሉ ግዙፍነት የሚሰጥ ወይንም የሚያጸና ቁስ አካል እንዲሆኑ የሚያደርግ አናሥር በተመለከተ ሰጥተዉት የነበረው ሥነ ጥናታዊ መላ ምት መሠረት በማድረግ የተከናወነ ምርምር መሆኑም ሲገለጥ፣ አዲሱ ግኝት ይፋ ከተደረገበት ቀን በኋላ ከተለያዩ የጥናትና የሥነ እውቀት እንዲሁም የሥነ ምርምር ዘርፎች አስተያየት እየሰጠበት መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ ቶማስ፦ “ዘአኵይኖ፦ “ስለ ተፈጠሩ ነገሮች ትክክለኛ ሃሳብ ከሌለን ስለ እግዚአብሔር ትክክለኛ ሃሳብ ሊኖረን አይችልም” በማለት የገለጠው ሃሳብ የሚያስታውስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ወጣት ምእመናን ተቀብለው፣ የምናስበው እውን የሚሆነውና የተፈጥሮ ሁኔታ በጠቅላላ እንቆቅልሽ ነው ወይም አቢይ ተጋርጦ ነው ለሚለው ጥያቄ “ከፍ ያለ አንድ ተመሳሳይ አእምሮ ባይኖር ኖሮ አእምሮአችን ሌላውን ከእርሱ የተለየ አእምሮ መኖሩንም ለይቶ ለማወቅ ባልቻለ ነበረ”። ተስማሚ ባለ ቤታዊ የአእምሮ ብቃትና ጠቅላይ የእእምሮ ብቃት በቁስ አካል ውስጥ/ዘንድ መኖሩንም ሲያመለክቱ፦ “ዓለምን ባለን የአእምሮ ብቃት እንደ መሣሪያ ልንጠቀምበት የምንችል መሆናችን በበለጠ ስንረዳ፣ የተፈጥሮ እቅድ ግሃድ እይሆነ በበለጠ ይገለጥልናል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
በሁሉም ጅማሬ ዘንድ ያለው ልባም ፈጣሪ፣ የአእምሮ የበላይነት መግለጫ ነው ካልሆነ ግን ኢምክንያታዊነት የበላይነት እንዳለውና አእምሮ የኢምክንያታዊነት ውጤት ነው የሚለውን ሃሳብ ለመደገፍ እንገደዳለን ስለዚህ፦እነዚህን ሁለት አመለካከቶች ለይቶ ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውጤት የለውም፣ አማራጩ ምክንያት ላይ ማተኮረ ተገቢ ነው፣ አማራጩም ክርስትና የሚገልጠው ምክንያታዊነትና የእእምሮ ቀዳሚነት የሚለው መሠረታዊ ሃሳብ ነው። ይኽ አማራጭ የላቀ ተቀባይነት ያለው ምክንያት፣ ከሁሉ ነገር በስተጀርባ አንድ ትልቅ እማኔ ልስጠው የሚገባን ምክንያት/አእምሮ እንዳለ ያረጋግጥልናል” በማለት በሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት በጥልቅ እንዳብራሩትም የቅድስት መንበር መግለቻጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.