2012-07-06 13:30:59

ብፁዕ ካርዲናል ፒያቸንዛ፦ “ሥልጣናዊ የቤተ ክርስትያን ትምህርት ያለው የትምህርት አሰጣጥ ወይንም የሕንጸት ቀውስ ለማስወገድ የሚያበቃ መንገድ ጠቋሚ ነው”።


ለዘርአ ክህነት ተማሪዎችና ለውሉደ ክህነት ቀጣይ ሕንጸት ቤተ ክርስትያንን ከሚመራው ሥልጣናዊ ትምህርት ውጭ ለማረጋገጥ የሚቻል አይደለም። ማንም የዘርአ ክህነት የሕንጸት ኃላፊ ወይም አስተማሪ የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት እንደ አማራጭ ወይንም የገዛ እርሱ እውቀት ከቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት RealAudioMP3 በላይ አድርጎ ማቅረብ እንደሌለበት በ 22ኛው ዓለም አቀፍ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች አለቆችና የሕንጸት ኃላፊዎች ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የካህናት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማውሮ ፒያቸንዛ ባሰሙት ንግግር እንዳብራሩ የገለጠው ዜኒት የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ይህ በዓለም አቀፍ ቅድስት ድንግል ማርያም እመ ቤተ ክርስትያን ጳጳሳዊ ተቋም በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ከ 96 አገሮች የተወጣጡ ከ672 ሰበካዎች የተላኩ 1.490 ካህናት እየተሳተፉ መሆናቸው ገልጦ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የትምህርት አሰጣጥ ቀውስ በጠቅላላ ያለው የሕንጸት መቃወስ እንዲወገድ ቤተ ክርስትያን ለሰው ልጅ የምትሰጠው ልዩ ትኵረት በሰው ልጅ ሁኔታ ተካፋይ በመሆን ሰው ሰብአዊነቱን ለማልበስ እርሱም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከመገናኘት የሚረጋገጠው የተሟላ ሰብአዊነት ምክንያታዊነቱን በማስፋፋትና በማስተማር፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 እግዚአብሔር ፍቅር ነው በተሰየመው አዋዲ መልእክታቸው ቁጥር አንድ የገለጡት ሃሳብ ከአንድ ሁኔታ፣ አካል ጋር መገናኘት ማለት መሆኑ ማብራራታቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ብፁዕነታቸው አክለውም የሰብአዊነት ጥያቄ ከክርስቶስ ‘ሁኔታ’ ማገናኘት የተሰኘው ሃሳብ አስረድተው፣ ክርስቶስ በባህርዩ የኖረው እኛ በጸጋ ልንኖረው እንችላለን፣ የሚሰጠው ሕንጸት በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ ለተፈጠረው ሰው በመሆኑ፣ በሰው ልጅ ዘንድ ያለው አርአያና አምሳያ ማእከል ያደረገ መሆን አለበት እንዲህ ሲሆን ብቻ ነው ለሰው ልጅ ሰብአዊነቱን ለማጎናጸፍ የሚቻለው። የዚህ አርአያና አምሳያ ፍጹም አብነትም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንዳሉ ዜኒት የዜና አገልግሎት አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.