2012-07-05 11:32:35

ር ሊ ጳ በነዲክት በሊባኖስ ሐዋርያዊ ዑደት ያካሄዳሉ ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ፊታችን ወርሃ መስከረም እኤአ አስራ አራት ቀን በሊባኖስ ለሶውስት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት ለማካሄድ ከሐውርያዊ መንበራቸው እንደሚነሱ የቫቲካን የዜና ምንጭ ተቋም ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁ የዜና ምንጭ ተቋም ዘገባ መሰረት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲት ከመስከረም 14 ቀን ኣስከ 16 ሊባኖስ ውስጥ ሐዋርያዊ ዑደት ያካሄዳሉ ።

ሐዋርያዊ ጉብኝቱ የመካከለኛው ምሥራቅ ጳጳሳት ድሕረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ትኩረት የሰጠ እንደሆነም የዜና ምንጩ አስታውቀዋል። ቅድስነታቸው በሊባኖስ የየሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሃገራት አቀፍ 24ኛ ሐዋርያዊ ዑፍደት መሆኑ ነው ።

የበነዲክት 16ና የሊባኖስ ሐዋርያዊ ዑደት መርሃ ግብር እንደሚያመለክተው ፡በነዲክት 16ኛ መስከረም 14 ቀን እኤአ ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ይነሳሉ በየሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኃላ ሁለት ሰዓት ላይ በይሩት ራፊቅ ሐሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ ።

ከራፊቅ ሐሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሀሪሳ ከተማ ተጉዘው እዚያው በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ካተድራል የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳኑ ይፈርማሉ በማለት የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው መርሃ ግብሩ አስገንዝበዋል።

መስከረም 15 ቀን በነዲክት 16ኛ መስከረም 15 ቀን ጥዋት ወደ ባብዳ ቤተ መንግስት ተጉዘው ለሀገሪቱ ርእሰ ብሔር የክብር ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተያይዞ ተገልጠዋል።

በመቀጠልም ከየሃይማኖት ማህበረ ሰቦች አባቶች ከየውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ከየመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚገኛኑም ተመልክተዋል።

እኩለ ቀን ላይ ከየሊባኖስ ፓትርያርካት ከጳጳሳት እና ከየመካከለናው ምስራቅ የጳጳሳት ሲኖዶስ ልዩ ምክር ቤተ አባላት ጋር በጋራ ለምሳ እንደሚቀመጡ የሊብኖስ ሐዋርያዊ ዑደታቸው መርሃ ፕሮግራም አስታውቀዋል።

የምሳ ሥርዓት የሚከናወንበት መካን በሊባኖስ በዞማር ከርከ የአርመን ካቶሊክ ፓትርያርክ ቤተ ፕትርክና እንደሆነም ተገልጠዋል።

ከቀትር በኃላ ቤተ ፕትርክና አጠገብ በሚገኘው አደባባት ከሀገሪቱ ወጣቶች ጋ እንድመገኛኙ እሁድ መስከረም 16 ቀን እኤአ beirut city center waterfront የበይሩት ከተማ ማእከል ዎተርፍሮንት ሥርዓተ ቅዳሴ እንድሚመሩ እና እዚህ የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለክልሉ ጳጵሳት እንደሚያስረክቡ ከወዲሁ ተነግረዋል።

በሀሪሳ ቤተ ሐዋርያዊ ጵጵስና ከፓትርያርካት እና ጳጵሳት ተሰናብተው ለተደረገላቸው መስተንግዶ አመስገነው ወደ ቫቲን ለመመለስ በይሩት ራፊቅ ሐሪሪ አውርፕላን ማረፍያ እንደምያቀኑ እና አምሻቸው ሮም እንደሚገቡ የቫቲካን የዜና ምንጭ ተቋም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.