2012-07-04 14:16:33

የዓለማውያን ምእመናንና የውልደ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት


አስፍሆተ ወንጌል ለአሕዛብ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ ከትላትና በስትያ የዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይፋዊ ምሉእ ጉባኤ RealAudioMP3 ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ በአገሪቱ የሚታየው የጥሪ እድገት እግዚአብሔር ለአገሪቱና በአገሪቱ አማካኝነትም ለዓለም የሚሰጠው ጸጋ ነው በማለት፣ ቤተ ክርስትያን በአባላቷ አማካኝነት በዕለታዊ ኑሮ ተጨባጭ በመሆን በቤተ ክርስትያን ሕይወትና ተልእኮ በመሳተፍ ይኸንን ኃላፊነት በመኖር የሚሰጡት ምስክርነት ለክህናት፣ ለገዳማዊ ሕይወት ጥሪ እድገት ምክንያት ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ቤተ ክርስትያን በሕዝብ ሕይወት ንቁ ተሳታፊ በመሆን በተለያየ ዘርፍ የምትሰጠው አገልግሎት ለተሟላ የሰብአዊና መንፈሳዊ እድገት መሠረት መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ በማብራራት፣ በኮንጎ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በሕዝቡ ዕለታዊ ሕይወት ንቁ ተሳታፊ በመሆን በተለያየ መስክ ሕንጸት በማቅረብ ለተሟላ ሰብአዊ እድገት የምትሰጠው አገልግሎት የሚመሰገን ቢሆንም፣ ጥሪ ነውና ለዚህ ጥሪ የሚያበቃው ጠሪው እግዚአብሔር እናመስግን። በቤተ ክርስትያንዋ ለዓለማውያን ምእመናንና ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት በበለጠ ተነቃቆት እንዲቀርብም በማሳሰብ ምእመናን ለብፁዓን ጳጳሳት የሚሰጡት ታማኝነት ብፁዓን ጳጳሳት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ካላቸው ኅብረት የመነጨ እግዚአብሔር በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት በሰጣቸው ሐዋርያዊ ኃላፊነት ላይ የጸና ነው። ስለዚህ እውነትንና ለጋራ ጥቅም አገልግሎት የሚሰጡት ነቢያዊና ሓዋርያዊ አገልግሎት እንዲቀጥሉበት ማበረታታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.