2012-07-04 14:11:15

የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤትና የመክሲኮ ሕዝባዊ ምርጫ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ አንድ ቀን 2012 ዓ.ም. በመክሲኮ የተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ አሸናፊ የሆነው መክሲኮን እ.ኤ.አ. ከ 1929 እስከ 2000 ዓ.ም. በቀጣይነት አገሪቱን ለረዥም ሰባ አንድ ዓመታትRealAudioMP3 የመራው አብዮታዊ ተቋም የተሰየመው የፖለቲካ ሰልፍ ማሸነፉ ሲገለጥ፣ የፖለቲካው ሰልፍ መሪ ኤንሪከ ፒኛ ኒየቶ ርእሰ ብሔር እንዲሆኑ ያበቃው ሕዝባዊ ድምጽ እንዲከበርና ፈጽሞ እንዳይካድ የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 ለአዲሱ ርእሰ ብሔር የአደራ ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ሕዝብ የሚሰጠው እማኔ በአዲሱ መንግሥት እንዳይካድ የአደራ ጥሪ የሚያስተጋባው የብፁዓን ጳጳሳት መልእክት፣ የዴሞክራሲው ሂደት ለሰላም ለፍትሕና ለእድገት መሠረት መሆኑ የሚያብራራ ሲሆን፣ ነጻ ምርጫ የሕዝብ ፈቃድና ፍላጎት የሚያጎላ በመሆኑም መንግሥት ሕዝብ ለሰጠው አደራ ብቁና ንቁ ሆኖ እንዲያገለግል የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ካርሎስ አጉይራና የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ቪክቶር ረነ ሮድሪገዝ ጎመዝ ፊርማ የተኖረበት መልእክት፣ የሕዝብ ፍላጎት ለፖለቲካ መርሃ ግብር መሠረት መሆን አለበት እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በመክሲኮ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ክሪስቶፍ ፒየር የመክሲኮ ሕዝባዊ ምርጫና ወጤቱ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ያካሂዱት ቃለ ምልልስ ያጠናቀረው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ እንዳመለከተቱ፣ በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ የሆነው አብዮታዊ ተቋም የፖለቲካ ሰልፍ እ.ኤ.አ. መክሲኮን ከ 1929 እስከ 2000 ዓ.ም. የመራው ዳግም ወደ ስልጣን የጠራ አይደለም፣ የፖለቲካው ስለፉ ታድሶ እና ከወቅቱ የዴሞክራሲው ሥርዓት ጋር የተስማማ መሆኑ ነው የሚያመለክተው። ስለዚህ የነበረው አምባገነናዊ አመለካከት ዳግም የሚያነቃቃ ሊሆን አይችልም ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን የማንም የፖለቲካ ሰልፍ ደጋፊና ለማንም የፖለቲካ ሰልፍ ቅርብ አትሆንም፣ ስለዚህ መሠረታውያን እሴቶች እንዲጠበቁና በሙላት እንዲከበሩ በፖለቲካው በኤኮኖሚና በማሕበራዊው ዘርፍ ሰብአዊነት ማእከል እንዲሰጠው የሚል ራዕይ በማሰማት፣ ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የተሰኘው የሕይወት ባህል እንዲስፋፋ፣ ለስደተኞችና ለተናቁት ለድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ትብብርና ደጋፍ እንዲሰጥ፣ በጠቅላላ ሰብአዊነት እንዲከበር በማስተማር የሕዝብን ኅሊና በማነቃቃቱ ሂደት አስተዋጽኦ በመስጠት፣ የሐይማኖት ነፃነት እንዲከበር ጥሪ ታቀርባለች ካሉ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. እስከ 1992 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በመክሲኮ ሕጋዊነት እውቅና እንዳልነበራት አስታውሰው፣ ገና ብዙ መረጋገጥ የሚገባቸው አስፈላጊ ጉዳዮች ያሉ ቢሆንም ቅሉ፣ ቤተ ክርስትያን ውይይትና መተባበር የሚለው ዓላማ በመከተል መፍትሔ እንዲያገኙ አበክራ ከመንቀሳቀስና ከማገልገል ወደ ኋላ እንደማትል ነው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.