2012-07-04 14:13:00

ከፍርሃት በኋላ ተስፋ


የኢጣሊያ ብሔራዊ የትብብር ጉዳይ ሚኒ. አንድረያ ሪካርዲ ወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ባላቸው እምነትና በሥነ ታሪክ ሊቅነት አማካኝነት በማንበብ ከፍርሃት በኋላ ተስፋ በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 ከሳምንታዊው ፋሚሊያ ክርስትያና የተሰየመው ካቶሊካዊ መጽሔት በተለያየ ወቅት ያቀረቡት ጽሑፍ ተጠቃሎ በቅዱስ ጳውሎስ ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ሲገለጥ፣ ይህ የዓለማዊ ትሥሥር ፍርሃት በሚል መጠሪያ ሚኒ. ሪካርዲ የለዩት ወቅታዊው ሰብአዊው ፍርሃት የዓለማዊ ትስስር ፍርሃትና የእምነት ተስፋ የሚያጎላ መሆኑ ሲነገር፣ ዓለማዊ ትስስር፣ ግለ ሰብአዊነት ተቋሞች መለያ ከሌላው ጋር ተነጻጻሮ መኖርን የሚያጎሉ ሲሆን፣ የተለያዩ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኙ በማለት የውይይት ባህል እዲስፋፋ በማድረግም የሰላም ባህል እንዲረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ባለው ኤኮኖሚያዊና ቁጠባዊ ቀውስ አማካኝነት እንዳይቋረጥ፣ ወቅታዊው ቀውስ ሥነ ምግባር በማስቀደም የሚፈታ መሆኑ ይጠቁማል።
የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒ. ማሪዮ ሞንቲ የሚኒ. ሪካርዲ መጽሓፍ ለንባብ በቀረበበት ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ ፍርሃት በድንገት ካንተ ርቆ የነበረው ከአንተ የተለየው አጠገብህ እንዳለ ከመገንዘብ የሚወለድ ነው። ማኅበራዊ ክስተቶች የሚባሉት ስደት፣ መፈናቀል የመሳሰሉት ሩቅ የነበረውን ቅርብ በሚያደርግ ባህል ልማድ በጠቅላላ የአንድ ኅብረሰብ ጠባይ በመንካት እንዲነጻጸር ከማድረጉም አልፎ በኤውሮጳ ተዋህዶ መኖርን ያነቃቃ ነው ሲሉ፣ የፊረንዘ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ በቶሪ በበኵላቸውም፣ ተስፋ ከፍርሃትና ከብቸኝነት የሚፈውሰን ያለብን ፍርሃትና የብቸኝነት ፈተና የሚገስጽ ነው። ተስፋ ከጦቢያ ወይንም ሊረጋገጥ ከማይችለው ምኞት ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የለውም። ምኞት በተጨባጩ ጊዜ እየተኖረ ነገር ግን ከተጨባጩ አለም ተለይቶ ለመኖር የሚገፋፋ የማይጨበጥ ባዶ ምኞች ሲሆን፣ ተስፋ ግን ካለው ተጨባጭ ጊዜ ሳያመልጥ፣ በተጨባጩ ሁኔታ ተጨባጩን ሁኔታ ወደ ተስፋ የሚመራ መንገድ ነው። ይህ ደግሞ አማኞች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ላላቸው እምነት መሠረት ነው ብለዋል።
የመጽሐፉ ደራሲ ሚኒ. ሪካርዲ፦ ተስፋ በጋራ መገንባት አለበት፣ የምንኖርበት ዓለት የተለያዩ ፍርሃቶች የሚገለጥበት፣ የጦርነት ፍርሃት፣ የብሩህ መጻኢ መጨለም የሚቀሰቅሰው ፍርሃት፣ የተለየው (ካንተ የተለየው) ጋር መገናኘት የሚወልደው ፍርሃት፣ ሩቅ የሚኖሩትንም መፍራት፣ በርግጥ የምንኖርበት ዓለም የተለያዩ ፍርሃቶች የከበቡት ነው የሚመስለው፣ ስለዚህ እነዚህን ፍርሃቶች ለማሸነፍ የሰላምና የውይይት እንዲሁም የሕይወት ባህል መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.